ሮቢንሆ በአስገድዶ መድፈር ወንጀል የ9 አመት የእስር ቅጣት ተፈርዶበታል
የቀድሞ የብራዚል ብሄራዊ ቡድን ተጫዋች ሮቢንሆ የተፈረደበት የእስር ጊዜ ለመፈጸም እስር ቤት መግባቱ ተገለጸ።
ሮቢንሆ በሚል ቅጽል ስሙ የሚታወቀው ብራዚላዊው ቦንሰን ዲ ሶውዛ በአስገድዶ መድፈር ወንጀል የ9 አመት የእስር ቅጣት ተፈርዶበታል።
ሮቢንሆ ጥፋኛ ተብሎ ቅጣቱ የተላለፈበት ከሁለት ዓመት በፊት በጣሊያን ውስጥ ነው የተባለ ሲሆን፤ በፈረንጆቹ. በ2013 ሚላን ውስጥ በሚገኝ የምሽት ክበብ የአልባኒያ ዜግነት ያላት ሴትን በቡድን በመድፈር ወንጀል ነው የተቀጣው።
የ40 ዓመቱ ብራዚላዊ ሮቢን በትውልድ ሀገሩ ብራዚል ውስጥ በምትገኘው ሳንቶስ ከተማ በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ በቁጥጥር ስር መዋሉም ተነግሯል።
የጣሊያን መንግስት ሮቢንፎ ተላልፎ ሊሰጠው ባለመቻሉ የተላለፈበትን የእስር ቅጣት በብራዚል ውስጥ እንዲፈጽም በተደጋጋሚ ስተይቅ ነበር ተብሏል።
የብራዚል ፍርድ ቤትም የጣሊያን ፍርድ ቤት ያሳለፈውን የቅጣት ውሳኔ ያጸና ሲሆን፤ ሮቢንሆ በቤት ውስጥ የቁም እስረኛ ከሚሆን ወደ ማረሚያ ቤት ወርዶ ቅጣቱን እንዲፈጽም ውሳኔ አሳልፏል።
የብራዚል የፍትህ ስርዓት በሮቢንሆ ላይ ያሳለፈው ውሳኔ በበርካታ መገናኛ ብዙሃን እና ተቋማት እየተወደሰ ይገኛል ተብሏል።
ለሀገሩ 100 ጨዋታዎችን ያደረገው የቀድሞው የብራዚል ብሄራዊ ቡድን ወንጀሉ በተፈፀመበት ወቅት ለኤሲ ሚላን እየተጫወተ ነበር።
ከጣሊያን መልስ በማንቸስተር ሲቲ ለሁለት አመታት የቆየው ሮቢንሆ እሁድ እለት ለብራዚል መገናኛ ብዙሃን እንደተናገረው ከአልባኒያዊቷ ሴት ጋር ያደረገው ግንኙነት "ስምምነት" ነበር ብሏል።