ብራዚል በፈረንጆቹ 1958 እና 1962 በተከታታይ ባሸነፈቻቸው የአለም ዋንጫ ወድድሮች ዛጋሎ በክንፍ ላይ ተሰልፎ ተጫውቷል
የብራዚሉ የአራት ጊዜ የአለም ዋንጫ አሸናፊ ማሪዮ ዛጋሎ አረፈ።
ተጨዋች እና አሰልጣኝ በመሆን ለብራዚል አራት የአለም ዋንጫ ያሸነፈው አንጋፋው ተጨዋች ማሪዮ ዛጋሎ በ92 አመቱ ህይወቱ አልፏል።
ብራዚል በፈረንጆቹ 1958 እና 1962 በተከታታይ ባሸነፈቻቸው የአለም ዋንጫ ወድድሮች ዛጋሎ በክንፍ ላይ ተሰልፎ ተጫውቷል።
ዛጋሎ በአለም እጅግ ትልቅ ቡድን የተባለውን እነ ፔሌን፣ ጃርዚኒሆ እና ካርሎስ አልቤርቶን ያቀፈውን ቡድን በመምራት በ1970 ዋንጫ አንስቷል።
ዛጋሎ አሰልጣኝ ሆኖ በ1994 የመጨረሻውን ዋንጫ ባነሳበት ጨዋታ፣ ካርሎስ አልቤርቶ ፔሬራ ረዳት አሰልጣኙ ነበር።
ዛጋሎ በ1998ቱ የአለም ዋንጫ የብራዚልን ቡድን ለፍጻሜ ጨዋታ ማድረስ የቻለ ቢሆንም በአዘጋጇ ፈረንሳይ ሽንፈት ለማስተናገድ ተገዷል። ዛጋሎ ተጨዋች እና አሰልጣኝ በመሆን የአለም ዋንጫ በማንሳት የመጀመሪያው ሰው ነው።
"በታላቅ ሀዘን ውስጥ ሆነን የአራት ጊዜ የአለም ዋንጫ አሸናፊው ማሪዮ ጆርጅ ሎቦ ዛጋሎ ሞት እንነግራችኋላን" የሚል መግለጫ በይፋዊ የኢንስታግራም ገጹ ወጥቷል።
በኮከቦች ባሸበረቀው የብራዚል የእግርኳስ ታሪክ ውስጥ ዛጋሎ በጣም ወሳኝ ከሚባሉት አንዱ ነው።
ታዳጋ ሆኖ በ1950 በተካሄደው የአለም ዋንጫ ጨዋታ አስተናጋጇ ብራዚል ወሳኝ በሆነ የፍጻሜ ጨዋታ በኡራጓይ ስትሸነፍ በማራካና ስቴዲየም ከተመለከቱት 200ሺ ሰዎች ውስጥ አንዱ ነበር።
ዛጋሎ በ2013 ለቢቢሲ "ያን ቀን መቼም ከአእምሮየ አይጠፋም" ሲል ተናግሯል።
ዛጋሎ ለብራዚል መጫወት የጀመረው ከ1950 የአለም ዋንጫ ትንሽ ቀደም ብሎ በ26 አመቱ እንደነበር ተገልጿል።
የ1958ቱን የአለም ዋንጫ ካነሳው የቡድን አባላት ውስጥ የጨመረሻው በህይወት መቆየት የቻለው ዛጋሎ ነበር።
ፔሌ በ1962ቱ የአለም ዋንጫ መጀመሪያ አካባቢ ሲጎዳ ዛጋሎ ግን ተከላካይ መስመር ላይ መበሰለፍ ብራዚል ባልተጠበቀ ሁኔታ ቸኮዝሎቫኪን እንድታሸንፍ አስችሏታል።
ዛጋሎ ለሀገሩ 33 ዋንጫ በማስገኘት በ1965 ነበር ጫማ የሰቀለው።
ዛጋሎ በ38 አመቱ ጃኦ ሳልዳንሃን በመተካት የብራዚል ቡድን አሰልጣኝ ከመሆኑ በፊት የማሰልጠን ስራ የጀመረው በቦታፎጎ ነው።
አስልጣኝ ሆኖ የመጀመሪያውን በሜክሲኮ የተካሄደውን የአለም ዋንጫ ማንሳት ችሏል።
ዛጋሎ ከብራዚል ብሄራዊ ቡድን በተጨማሪ የኩየት፣ የሳኡዲ አረቢያ እና የአረብ ኢምሬትስ ብሄራዊ ቡድኖችን አሰልጥኗል።