ፔሌ ከብራዚል ብሔራዊ ቡድን ጋር 3 የዓለም ዋንጫዎችን ማሳት የቻለ ድንቅ ተጫዋች ነበር
ብራዚላዊው የእግር ኳስ ንጉስ ፔሌ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተሰምቷል።
የቀድሞ እግር ኳስ ተጫዋች ፔሌ በካንሰር ህመም ምክንያት ሆስፒታል ገብቶ ህክምና ሲከታተል የቆየ ሲሆን፤ በ82 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
በፈረንጆቹ በ 1940 የተወለደው ፔሌ እግር ኳስ ገና በልጅነቱ በአስራ አምስት ዓመቱ በሳንቶስ ክለብ በመጫወት መጀመሩ ይታወቃል።
- ብራዚል ግዙፉን ማራካኛ ስታዲየም በእውቁ ተጨዋች ፔሌ ስም ልትሰይም ነው
- ክርስቲያኖ ሮናልዶ የፔሌን ክብረወሰን መስበሩን ተከትሎ ከፔሌ የእንኳን ደስ አለህ መልእክት ደረሰው
በአራት የዓለም ዋጫዎች ላይ መጫወት የቻለው ፔሌ ከብራዚል ብሔራዊ ቡድን ጋር ሶሰት የዓለም ዋንጫዎችን ማንሳት የቻለ ድንቅ የእግር ኳስ ተጫዋች መሆኑ ይታወቃል።
ፔሌ በሳንቶስ ቆይታውም ከክለቡ ጋር ስድስት የሊግ ዋንጫ ፣ ሁለት ኮፓ ሊቤርታዶሬስ እና ሁለት ኢንተር ኮንቲኔንታል ዋንጫዎችን ማንሳት ችሏል
ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ አስተዳዳሪ አካለ ፊፋ ፔሌን ታላቁ ተጫዋች ሲል የሚጠራው ሲሆን፤ በፈረንጆቹ 2000 የአለም አቀፍ እግር ኳስ እና ታሪክ የምትዓመቱ የዓለማችን ምርጥ ተጫዋች ሽልማትን መቀዳጀቱም ይታወቃል።
ፔሌ በእግር ኳ ዘመኑ 1 ሺህ 228 ግቦችን ከመረብ ያሳረፈ ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ 77ቱ ለሀገሩ ብራዚል ያስቆጠራቸው ናቸው።