በቀድሞ ሚስቱ አመልካችነት ሞቷል የተባለው ሰው ከ28 ዓመት በኋላ በህይወት ተገኘ
ግለሰቡ ባደረገው እልህ አስጨራሽ ትግል በመጨረሻም የልደት ማስረጃውን በእጁ አስገብቷል
ግለሰቡ ሞተሃል በመባሉ ምክንያት ምንም አይነት አገልግሎት ለማግኘት ተቸግሮ ቆይቷል ተብሏል
በቀድሞ ሚስቱ አመልካችነት ሞቷል የተባለው ሰው ከ28 ዓመት በኋላ በህይወት ተገኘ፡፡
በብራዚሏ ቶካንቲንስ ክልል ውስጥ ይኖር የነበረው ግለሰብ ከ28 ዓመት በፊት ነበር በቀድሞ ባለቤቱ አማካኝነት ህይወቱ ማለፉ የተመዘገበው፡፡
የክልሉ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ የ71 ዓመቱ ማኑኤል ማርሲያኖ ዳ ሲልቫ የተባለው ብራዚሊያዊ በፈረንጆቹ 1995 ላይ በቀድሞ ሚስቱ አመልካችነት እና ሌሎች ምስክሮችን ከሰማ በኋላ መሞቱን አጽድቆ ነበር፡፡
ሞተህል የተባለው ይህ ግለሰብ ምርጫ እና ሌሎች የዜግነት አገልግሎቶችን ማግኘት አለመቻሉን ተከትሎ ነበር ጉዳዩን ለማጣራት የተገደደው፡፡
ቀስ በቀስም የጡረታ ክፍያውን እና የነጻ ህክምና አገልግሎቶችን ማግኘት ያልቻለው ይህ ግለሰብ በመጨረሻም በቀድሞ ባለቤቱ አማካኝነት ሞቷል ተብሎ መመዝገቡን ያውቃል፡፡
ብራዚል እና ቻይና ከዶላር ውጪ በሆነ ገንዘብ ለመገበያየት ተስማሙ
በህይወት መኖሩን ዳግም ለመንግስት አካላት ቢያመለክትም ሰሚ ያላገኘው ይህ አዛውንት ጠበቃ ለመቅጠር ተገዷል ተብሏል፡፡
ግለሰቡ በጠበቃው አማካኝነት ለሁለት ዓመታት ባደረጉት ጥረት ከ28 ዓመታት በኋላ የሞት ምዝገባው የተነሳለት ሲሆን አሁን የነጻ ህክምና፣ በምርጫ መሳተፍ እና የጡረታ ክፍያውን የማግኘት መብቱ እንደተጠበቀለት ተገልጿል፡፡
የግለሰቡ የቀድሞ ሚስት ለምን ሞቷል ማስባል እንደፈለገች ለጊዜው ያልተገለጸ ሲሆን ድርጊቱን ግን ሆን ብላ ስለማድረጓ ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል፡፡