ብሪክስ ኢትዮጵያን ጨምሮ 10 አባላት አሉት
ብሪክስ እና ጠቋሚ መረጃዎቹ
በብራዚል፣ሩሲያ፣ ሕንድ፣ ቻይና እና ደቡብ አፍሪካ የተመሰረተው ብሪክስ 16ኛ ጉባኤውን በሩሲያዋ ካዛን ከተማ እያካሄደ ይገኛል፡፡
በዚህ ጉባኤ ላይ ጥምረቱን አዲስ የተቀላቀሉት እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ሀገራት መሪዎችም በመሳተፍ ላይ ናቸው፡፡
በምዕራባዊያን የተያዘውን የዓለም ስርዓት ለመገዳደር እና ዓለማችን ተጨማሪ አዲስ ስርዓት ያስፈልጋታል በሚል የተቋቋመው ብሪክስ የ3 ነጥብ 25 ቢሊዮን ህዝብ ድርሻ አለው፡፡
የጥምረቱ አባል ሀገራት ዓመታዊ እድገት 26 ትሪሊዮን ዶላር የደረሰ ሲሆን በዓለማችን ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት እያስመዘገቡ ያሉ ሀገራትን በአባልነት ይዟል፡፡
ከ30 በላይ የዓለማችን ሀገራ አሁንም ብሪክስን ለመቀላቀል ጥያቄ እንዳቀረቡ የተገለጸ ሲሆን ከአንድ ዓመት በፊት ጥምረቱን ለመቀላቀል ጥያቄ ያቀረበችው አርጀንቲና ዳግም ከጥምረቱ አባልነት ራሷን ማግለሏ ይታወሳል፡፡