የ2015 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ልናውቃቸው የሚገባ እውነታዎች ምንድናቸው?
ፈተናው ከአንድ ወር በኋላ በመንግስት ዩንቨርሲቲዎች እንደሚካኬድ ተገልጿል
የዘንድሮውን ፈተና 870 ሺህ ገደማ ተማሪዎች ይፈተኑታል ተብሏል
የ2015 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና እውነታዎች።
እንደ ትምህርት ሚንስቴር ገለጻ ዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ፈተና ከሀምሌ 19 እስከ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ይካሄዳል።
በመንግሥት ዩንቨርሲቲዎች ይሰጣል የተባለው ይህ ፈተና የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በመጠናቀቅ ላይ መሆናቸውን ሚንስቴሩ አስታውቋል።
ከተፈታኞች መካከል 365 ሺህ 954 ያህሉ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ሲሆኑ ቀሪዎቹ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ናቸው ተብሏል።
በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍልን ከተፈተኑ 900 ሺህ ገደማ ተማሪዎች ውስጥ ወደ ዩንቨርስቲ ማለፊያ ውጤት ያመጡት 30 ሺህ አይሞሉም መባሉ አይዘነጋም።