በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ ባለው 15ኛ ጉባኤውም የአባላቱን ቁጥር ወደ 11 ለማሳደግ ወስኗል
“ብሪክ” (BRIC) የሚለውን ስያሜ ለመጀመሪያ ጊዜ ያስተዋወቀው ብሪታኒያዊው የኢኮኖሚ ባለሙያ ጂም ኦኔይል ነው።
ከብራዚል፣ ሩሲያ፣ ህንድ እና ቻይና ስያሜ የመጀመሪያ ፊደል ወስዶ “ብሪክ” የሚለውን ስያሜ ሲሰጥ በ21ኛው ክፍለዘመን ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት የሚያስመዘግቡ ሀገራት መሆናቸውን በመጥቀስ ነው።
የአራቱ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በፈረንጆቹ 2006 ሃምሌ ወር ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ በሩሲያ ሴንት ፒተርስበርግ ምክክር አድርገዋል።
“ብሪክ” የሚለው ስያሜ ጥቅም ላይ የዋለው ግን ሚኒስትሮቹ በመስከረም ወር 2006 ከመንግስታቱ ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ጎን ለጎን በኒውዮርክ ምክክር ሲያደርጉ ነው።
የመጀመሪያው የመሪዎች ጉባኤም በሰኔ ወር 2009 በሩሲያ አስተናጋጅነት መካሄዱ ይታወሳል።
“ብሪክ” ወደ “ብሪክስ” ያደገው ደቡብ አፍሪካ በ2010 በይፋ ቡድኑን ተቀላቅላ በ2011 የመጀመሪያው የመሪዎች ጉባኤ ላይ ስትሳተፍ ነው።
የአለማችን 40 በመቶ ህዝብ እና ከ30 በመቶ በላይ ኢኮኖሚ የሚይዙ ሀገራት ስብስብ የሆነው ብሪክስ ዛሬ ስድስት አዳዲስ አባላት እንዲቀላቀሉት ጋብዟል።
ከጥር 2024 ጀምሮ ብሪክስን የሚቀላቀሉት ሀገራት የቡድኑን አለማቀፍ ተጽዕኖ ለማሳደግ እንደሚያግዙ ይጠበቃል።
የብሪክስ የ15 አመት ጉዞን ይመልከቱ፦