ብሪክስን ለመቀላቀል ያለመከቱ ሀገራት እነማናቸው?
ብሪክስን ለመቀላቀል ያለመከቱ ሀገራት እነማናቸው?
ሩሲያ እና ቻይና ያሉበትን ጥምረት ለመቀላቀል አመልክተዋል፤ በርካቶችም ለማመልከት ፍላጎታቸውን እያሳዩ ይገኛሉ።
የእስያዎቹ ኃያላን ቻይናን እና ሩሲያ በመስራችነት የያዘው ብሪክን፣ በምዕራባውያን የባላይነት የሚመራውን የአለም ስርአት ለመቀየር ያለመ ነው።
የጥምረቱ መስራቾች ብራዚል፣ሩሲያ፣ ህንድ፣ ቻይና እና ደቡብ አፍሪካ ናቸው።
ብሪክስ ዶላርን ከገበያ ውጭ ሊያደርግ የሚችል አዲስ የጋራ መገበበያ ይፋ ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆናቸው ገልጿል።
ኢትዮጵያን ሶስት የአፍሪካ ሀገራት ጥምረቱን ለመቀላቀል ይፋዊ ማመልከቻ አስገብተዋል።
ሀገራት ብሪክስን ለመቀላቀል የሚፈልጉት አላስፈላጊ ከሆነ የምዕራባውያን ተጽዕኖ ለመላቀቅ እና አማራጭ የሆነ የብድር አቅርቦት ለማግኘት እንደሆነም ይነገራል።