የሀገሪቱ ማዕከላዊ ባንክ የገንዘብ ኖቶቹ ከፈረንጆቹ 2024 አጋማሽ ጀምሮ ለስርጭት ዝግጁ እንደሚሆኑ ተናግሯል
የእንግሊዝ ባንክ በፈረንጆቹ መስከረም 8 ፤ 2022 በዩናይትድ ኪንግደም ዙፋን ላይ የንጉስ ቻርለስ ሳልሳዊ ምስል የያዙ የመጀመሪያዎቹን የባንክ ኖቶች አስተዋውቋል።
የ74 ዓመቱ ንጉስ የሀገሪቱን ዙፋኑን ከእናታቸው ከንግሥት ኤልሳቤት ዳግማዊ ወርሰዋል።
የእንግሊዝ ባንክ የንጉስ ቻርለስ ሳልሳዊን ምስል የያዙት እነዚህ የገንዘብ ኖቶች ከላስቲክ መሰራታቸውን ተናግሯል።
የገንዘብ ኖቶቹ ከፈረንጆቹ 2024 አጋማሽ ጀምሮ ለስርጭት ዝግጁ እንደሚሆኑ የተነገረ ሲሆን፤ ከሚቀጥለው ዓመት አጋማሽ ጀምሮ በብዛት መመረት ይጀምራሉ ተብሏል።
የብሪታንያ ማዕከላዊ ባንክ ትናንት ሰኞ ባወጣው መግለጫ የንጉሱ ምስል የባንክ ኖቶች ንድፍ ላይ ማሻሻያ ሳይደረግ በ 5 ፣ 10 ፣ 20 እና 50 ፓውንድ ስተርሊንግ ኖቶች ላይ ይታተማል።
የንጉስ ቻርለስ ምስል የእናታቸውን ምስል በሳንቲሞች ፊትና ጀርባ ይተካሉም ተብሏል።
እንደ አጃንስ ፍራንስ ፕረስ ዘገባ የብሪታንያ ማዕከላዊ ባንክ ቃል አቀባይ በዚህ ገንዘብ ላይ የታተመው ምስል በፈረንጆቹ 2013 በንጉሳዊ ቤተሰብ የቀረበ ምስል ነው። ይህም ንጉሱ የመጨረሻውን ምስል ማጽደቁን ያሳያል ነው ያለው ።
የእንግሊዝ ባንክ የንግስት ኤልሳቤትን ምስል የያዙ የባንክ ኖቶች ከአዲሶቹ ሳንቲሞች ጋር በትይዩ መሰራጨታቸውን እንደሚቀጥሉ አመልክቷል።
በብሪታንያ በአሁኑ ጊዜ የሟች ንግሥት ኤልሳቤት ዳግማዊ ምስል የያዙ ወደ 27 ቢሊዮን የሚጠጉ ሳንቲሞች አሉ።
ሳንቱሞቹ ካልተበላሹ ወይም ካልተጎዱ በስተቀር እንደማይተኩ ተነግሯል።