የብሪታንያ ወንጀል ሚኒስትር ስለ ወንጀል መጨመር መግለጫ እየሰጡ እያለ የእጅ ቦርሳቸው ተሰረቀ
ሚኒስትሯ በብሪታንያ ስለጨመረው የስርቆት ወንጀል ከፖሊሶች ጋር መግለጫ በመስጠት ላይ ነበሩ
በብሪታንያ አጠቃላይ የወንጀል ምጣኔ እየቀነሰ ቢሆንም የንጥቂያ ወንጀል ግን በ40 በመቶ ጨምሯል
የብሪታንያ ወንጀል ሚኒስትር ስለ ወንጀል መጨመር መግለጫ እየሰጡ እያለ የእጅ ቦርሳቸው ተሰረቀ፡፡
የዓለማችን ዋነኛ የንግድ ስምምነቶች ከሚፈጸምባቸው ከተሞች መካከል አንዷ በሆነችው ለንደን ከተማ የስርቆጥ ወንጀሎች እየጨመሩ ይገኛሉ፡፡
በተለይም በሀገሪቱ መዲና ለንደን ከተማ ውስጥ የእጅ ስልክ፣ ቦርሳ እና በቀላሉ በእጅ የሚዙ ንብረቶችን ቀምተው በሞተር እና በሩጫ የሚመልጡ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው ተብሏል፡፡
የዚህ ወንጀል መጨመር ያሳሰባቸው የሀገሪቱ ፖሊስ እና ወንጀል ሚኒስትር ዲያና ጆንሰን በዚሁ ስርቆት ወንጀል መጨመር ዙሪያ መግለጫ እየሰጡ እያለ ቦርሳቸውን በሌቦች ተሰርቀዋል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ሲም ካርድ በመቀየር ስለሚሰራው የማጭበርበር ወንጀል ምን ያህል ያውቃሉ?
እንደ ዘገባው ከሆነ ሚኒስትሯ የሀገሪቱ ከፍተኛ ወንጀል መርማሪዎች እና የወንጀል መከላከል ኦፊሰሮችን ከሰበሰቡና ወንጀሉን ማስቆም እንዳለባቸው ማሳሰቢያ ከሰጡ በኋላ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
ይሁንና መግለጫውን ከጨረሱ በኋላ የእጅ ቦርሳቸውን ቢፈልጉ ሊያገኙት አልቻለም የጠባለ ሲሆን ጉዳዩ አግራሞትን ፈጥሯል፡፡
ፖሊስ ቆይቶ ባደረገው ክትትል የ56 ዓመት እድሜ ያለው አንድ ተጠርጣሪ የሚኒስትሯን ቦርሳ እነደሰረቀ ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ውሏል ተብሏል፡፡
ዩጎቭ የተሰኘው የጥናት ተቋም እንዳስታወቀው በብሪታንያ የሀገሬው ዜጋ በፖሊስ ላይ ያለው ዕምነት እየቀነሰ መጥቷል ብሏል፡፡
ግማሽ ያህሉ ብሪታንያውያን የሀገራቸው ፖሊስ ወንጀሎችን ያስቆማል የሚል ዕምነት የላቸውም የተባለ ሲሆን የሀገሪቱ ወንጀል እና ፖሊስ ሚኒስቴር ለወንጀል መከላከል ኦፊሰሮች ስልጠና ለመስጠት ማቀዱን አስታውቋል፡፡