የብሪታኒያው ካሪም ካሀን የአይሲሲ አቃቤህግ በመሆን ለ9 አመታት እንዲያገለግል ተመረጠ
አቃቤ ህግ ካሪም ተመድ በአይኤስ አይኤስ ላይ ያካሄውን የወንጀል ምርመራ በቡድን መሪነት መርቶ ነበር
አይሲሲ በአፍጋኒስታን በአሜሪካ ወታደሮች የሚፈጸመውን ወንጀል ለመመርመር ሲዘጋጅ ፕሬዘዳንት ትራምፕ በአይሲሲ ሰራተኞች ላይ ማእቀብ ጥለው ነበር
የብሪታኒያው ካሪም ካሃን በምስጥራዊ የድምጽ ምርጫ ሶስት ተቀናቃኞቹን አሸንፎ ነው መሪ አቃቤህግ የነበሩትን ፋቶ ቤንሶዳን ተክቶ የኢንተርናሽናል ክሪሚናል ኮርት(አይሲሲ) አቃቤ ህግ የሆነው፡፡
123 አባላት ያሉት ከ20 አመታት በፊት ስራውን የጀመረው መቀመጫውን ሃጉ ያደረገው ፍርድቤት የጦር ወንጀልን፣ የሰብአዊ መብት ጥሰት፣ዘርማጥፋትንና የወረራ ወንጅልን ያያል፡፡የብሪታኒያው አቃቤ ህግ ካሪም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) በአይኤስ አይኤስ ላይ ያካሄውን የወንጀል ምርመራ በቡድን መሪነት መርቶ ነበር፡፡
በ27 አመት የህግ ባለሙያነት ካህን ለብዙዎች አለምአቀፍ የወንጀል ችሎቶች በአቃቤህግነት፣እንደ ተከላከያና ለተጠቂዎች በማማከር ሰርቷል፡፡ ካህን በአይሲሲ የሚታወቁት መሪ የተከሳሽ ጠበቃ በመሆን ሲሆን ከኬንያ፣ከሱዳንና ሊቢያ በመጡ ጉዳዮች ላይ ሰርቷል፡፡
የአይሲሲን ትልቅ ስራ ለማግኘት ከፍተና ውድድር ተካዷል፡፡ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዋና አቃቤ ህጉን ቤንሶዳን ጨምሮ በኤይሲሲ ሰራተኖች ላይ ማእቀብ ጥሎ ነበር፡፡ ትራምፕ ማእቀቡን የጣሉት አይሲሲ በአፍጋኒስታን በአሜሪካ ወታደሮች የተፈጸመውን የጦር ወንጅል አይሲሲ ለመመርመር መዘጋጀቱ ተከትሎ ነበር፡፡
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ ባለፈው እንዳላው አዲሱ የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን በአይሲሲ ላይ የተጣለውን ማእቀብ በጥልቀት እንደሚመረምረው መግለጻቸው ይታወሳል፡፡ ባለፈው ሳምንት ፍ/ቤቱ ፍሊስጤም የሚፈጸመው የጦር ወንጅል ይመለከታኛል ብሎ ነበር፤ነገርግን አሜሪካና እስራኤም በጽኑ ይቃወሙታል፡፡