እንግሊዝ የመጀመሪያዎቹን ፈቃደኛ ጥገኝነት ጠያቂዎች ወደ ሩዋንዳ ላከች
የእንግሊዝ መንግስት በፍቃደኝነት ወደ ሩዋንዳ ለሚመለሱ ሰደተኞች ለእያንዳንዳቸው 3ሺ ዶላር እንደሚሰጥ ገልጿል
እንግሊዝ በፈቃደኝነት ላይ በተመሰረተው መርሃግብሯ የመጀመሪያዎቹን ጥገኝነት ጥያቄዎችን ወደ ሩዋንዳ መላኳ ተገለጸ
እንግሊዝ የመጀመሪያዎቹን ፈቃደኛ ጥገኝነት ጠያቂዎች ወደ ሩዋንዳ ላከች።
እንግሊዝ በፈቃደኝነት ላይ በተመሰረተው መርሃግብሯ የመጀመሪያዎቹን ጥገኝነት ጠያቂ ስደተኞችን ባለፈው ሰኞ እለት ወደ ሩዋንዳ መላኳን ሮይተርስ ዘሰን ጋዜጣን ጠቅሶ ዘግቧል።
ዘገባው ወደ ሩዋንዳ በርረዋል የተባሉት ሰደተኞች ማንነት ግልጽ አለመሆኑንም ጠቅሷል።
ይህ በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተው ሰደተኞችን የማስወጣት መርሃግብር እንግሊዝ በሚቀጥሉት ወራት በግዴታ ለማስወጣት ካቀደችው እቅድ የተለየ ነው።
ሩዋንዳ ፤ በብሪታኒያ የሚገኙ ጥገኝነት ጠያቂዎችና ስደተኞችን ተቀብላ ለማስተናገድ ተስማማች
እንግሊዝ በፍቃደኝነት ወደ ሩዋንዳ ለመሄድ ፍቃደኛ የማይሆኑትን በግዴት የምታስወጣው በእንግሊዝ ቻናል በኩል በትንንሽ ጀልባዎች ወደ እንግሊዝ ለመግባት የሚሞክሩ ሰደተኞችን ለማስቆም ነው።
የእንግሊዝ መንግስት በፍቃደኝነት ወደ ሩዋንዳ ለሚመለሱ ሰደተኞች ለእያንዳንዳቸው 3ሺ ዶላር እንደሚሰጥ ገልጿል። ስደተኞች እንግሊዝን ለቀው ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ የገንዘብ ድጋፍ የሚሰጣቸው ቢሆንም በዚህ እቅድ ግን ገንዘቡ የሚሰጣቸው በሩዋንዳ ለመኖር ሲስማሙ ነው።
የመንግስት ቃል አቀባይ እንደገለጹት ከሩዋንዳ መንግስት ጋር ባላቸው የስደተኞች እና የኢኮኖሚ ትብብር ስምምነት መሰረት ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ መላክ ችለዋል።
"ይህ ስምምነት በእንግሊዝ የስደተኝነት ሰነድ የሌላቸው ሰዎች ህይወታቸውን በሰላም ወደሚመሩበት ሰላማዊ ሶስተኛ ሀገር እንዲሸጋገሩ አስችሏል" ብለዋል ቃል አቀባዩ።
ከፈረንጆቹ 2018 ጀምሮ ከጦርነት እና ረሃብ በመሸሽ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች በትናንሽ ጀልባዎች ተጉዘው እንግሊዝ ገብተዋል።
መንግስት ስደተኞችን ከእንግሊዝ 6400 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ወደምትገኘው ሩዋንዳ ለመላክ ሲነሳ ያጋጠመውን የህግ እና የፖለቲካ ተቃውሞ ለማሸነፍ ሁለት አመት ፈጅቶበታል
በመጨረሻም ፓርላማው ከፋፋይ የተባለውን እቅድ ባለፈው ሳምንት አጽድቆታል።