ኔታንያሁ በቴላቪቭ የተነሳውን ሁከት ተከትሉ ኤርትራዊያን ስደተኞችን ሊያባርሩ ይችላሉ ተባለ
በእስራኤል በሚኖሩ የኤርትራ ጥገኝነት ጠያቂዎች መካከል በተከሰተ ግጭት ከ160 በላይ ሰዎች ተጎድተዋል
ጠ/ሚኒስትር ኔታንያሁ በእስራኤል የኤርትራ ጥገኝነት ጠያቂዎች በተነሳው ረብሻ ዙሪያ ዛሬ ከሚኒስትሮቻቸው ጋር ይመክራሉ
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በቴላቪቭ የተነሳውን ግርግር ተከትሉ ኤርትራዊያን ስደተኞችን ሊያባርሩ ይችላሉ ተባለ።
በእስራኤል ቴል አቪቭ በመኒኖሩ ኤርትራውያን መካከል በትናትናው እለት በተቀሰቀሰው ግጭት በትንሹ 160 ሰዎች መጎዳታቸው ተሰምቷል።
በግጭቱ ጉዳት ከደረሰባቸው ሰዎች መካከል ቢያንስ ስምት ኤርትራውያን ስደተኞች ከፖሊስ በተተኮሰ ጥይት ተመተው ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው የተገለፀ ሲሆን፤ 50 የእስራኤል ፖሊስ አባላትም መጎዳታቸው ተገልጿል።
ግጭቱ የተቀሰቀሰው በቴል አቪቭ የኤርትራ ኤምባሲ ያዘጋጀውን ዝግጅት በመቃወም የወጡ በመቶ የሚቆጠሩ ጥገኝነት ጠያቂ ኤርትራውያን ከፖሊስ ጋር ተጋጭተው እንደሆነም ጄሩሳሌም ፖስት ዘግቧል።
የእስራዔል ፖሊስ ሁከቱን መቆጣጠሩን እና ከተማዋን ማረጋጋቱን በመግለጽ፤ ከርብሻ ጋር በተያያዘ 39 ሰዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉንም አስታውቋል።
ይህንን ተከትሎም የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በትናትናው እለት ኤርትራውያን ጥገኘነት ጠያቂዎች ባስነሱት ረብሻ ዙሪያ በዛሬው እለት ከሚኒስትሮች ግብረ ኃል ጋር እንደሚመክሩ ይጠበቃል።
ሁከት ፈጣሪዎችን ህገ-ወጥ ነዋሪ መሆናቸውን የገለጸው መግለጫው፣ ግብረ ሃይሉ በሁከት ፈጣሪዎች ላይ፣ ከአገር ማባረርን ጨምሮ ሌሎች እርምጃዎችን ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚሰራም ተመልክቷል።
በቅርቡ በስዊድን ስቶኮልም በተዘጋጀ የኤርትራዊያን በዓል ላይ ሁከት ተከስቶ ሰዎች መጎዳታቸው ይታወሳል።
በስዊድን መዲና በተካሄደው በዚህ በዓል ላይ ለመሳተፍ በስፍራው ተገኝተው እያለ የፕሬዝዳንት ኢሳያስ ደጋፊ እና ተቃዋሚ ናቸው የተባሉ ኤርትራዊያን መካከል
በተመሳሳይ ከአንድ ወር በፊት በጀርመን በተካሄደ ተመሳሳይ የኤርትራ ባህላዊ በዓል ላይ በተፈጠረ ሁከት 26 የጀርመን ፖሊሶች መጎዳታቸው ይታወሳል።
በዚህ በዓል ላይ ግጭት ውስጥ የገቡት የፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ደጋፊዎች እና ተቃዋሚዎች መካከል ተከስቶ በርካታ ኤርትራዊያን ተጎድተውም ነበር።