ሩዋንዳ ፤ በብሪታኒያ የሚገኙ ጥገኝነት ጠያቂዎችና ስደተኞችን ተቀብላ ለማስተናገድ ተስማማች
ስምምነቱ፤ ህገወጥ ስደትን ለመቆጣጠር ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ላለቸው እንግሊዝ ትልቅ ፋይዳ ያለው ነው
በሩዋንዳና በብሪታኒያ መካከል የተፈረመው ስምምነት 157 ሚሊየን ዶላር የሚደርስ ነው ተብሏል
ሩዋንዳ ፤ በብሪታኒያ የሚገኙ ጥገኝነት ጠያቂዎችን እና ስደተኞችን ለማስተናገድ የሚያስችል የሚልየን ዶላሮች ስምምነት መፈራረሟ ተገለፀ።
ስምምነቱ፤ ህገወጥ ስደትን ለመቆጣጠር ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ላለቸው ብሪታኒያ ትልቅ ፋይዳ እንዳለውም ነው የተገለጸው።
የሩዋናዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቪንሴንት ቢሩታ “ሩዋንዳ ጥገኝነት ጠያቂዎችን እና ስደተኞችን ለማስተናገድ እንዲሁም ህጋዊ የመኖሪያ አማራጮችን ለማቅረብ ከእንግሊዝ ጋር የሚደረገውን ትብብር በደስታ ትቀበላለች” ብለዋል።
አሁን የተደረሰውና አስከ 157 ሚሊየን ዶላር የሚሸፍነው ስምምነት፤ ስደተኞች ከሩዋንዳዉያን ጋር ተቀላቅለው ለመኖር የሚያስችል ነው ተብሎለታል።
"ስምምነቱ የስደተኞችን ደህንነት እና ክብር የሚያስጠብቅ እንዲሁም የመኖር ፍላጎት ካላቸው በቋሚነት እንዲሰፍሩ መብት የሚሰጥ ነው" ብለዋል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ብሩታ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ መግለጫ የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን፤ መንግስታቸው ህገ-ወጥ ስደትን ለመግታት ያላቸውን እቅድ ይፋ ካደረጉበት ንግግር ከሰዓታት በፊት የተሰጠ ነው።
ጆንሰን ህገ-ወጥ ስደትን ለመግታት በገቡት ቃል ኪዳን በከፊል ቢመረጡም፤ ህገ-ወጥ ስደት በእሳቸው የስልጣን ዘመን በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ ይነገራል።
እንግሊዝ ፤ ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች በተለይም ከአፍሪካ የሚመጡ ስደተኞች በጥገኝነና በስደተነኝነት የሚኖርባት ሀገር መሆኗ ይታወቃል።