የእንግሊዝ ሰብአዊ መብት ድርጅት ሪፖርት በኳታር በሰራተኞች ላይ የሚደርሰውን ግፍ አጋለጠ
ስደተኛ የሆኑ ሰራተኞች ደሞዛቸው እንደተቀነሰባቸው ጥናቱ ጠቅሷል
በኳታር 2ሚሊዮን አካባቢ ከደቡባዊ ኢሲያ የመጡ ሰራተኞች ከኳታሩ 2022 የአለም ዋንጫ ጋር ተያያዥነት ባላቸው የግንባታ ስራዎች ተሰማርተው ሲሰሩ ነበር
በኳታር 2ሚሊዮን አካባቢ ከደቡባዊ ኢሲያ የመጡ ሰራተኞች ከኳታሩ 2022 የአለም ዋንጫ ጋር ተያያዥነት ባላቸው የግንባታ ስራዎች ተሰማርተው ሲሰሩ ነበር
የእንግሊዝ የሰብአዊ መብት ድርጅት እንዳጋለጠው በኳታር የሚገኙ ኩባንያዎች ስደተኛ ከሆኑ ሰራተኞች ደሞዝ እንደሚቀንሱና በዚህ ምክንያትም ሰራተኞቹ ለምግብ እየለመኑ ነው፡፡
ዘጋርዲያን የተሰኘው የእንግሊዙ ጋዜጣ ኢኩዲየም የተባለውን የሰብአዊ መብት ቡድን ጠቅሶ እንደዘገበው የኮሮና ቫይረስ ከተከሰተ በኋላ በኳታር ያሉ ኩባንያዎች በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠር ዶላርን ለሰራተኞች መክፈል እንዳልቻሉ ገልጿል፡፡
መቀመጫውን ሎንደን ያደረገው ይህ ቡድን በሺ የሚቆጠሩ ሰራተኞች ያለማስጠንቀቂያ መሰናበታቸውንና ደሞዛቸውን እንደተቀነሰባቸው እንዲሁም ያለክፍያ እረፍት እንዲወጡና ወደ ሃገራቸው የሚመለሱነትን ክፍያ ተገደው እንደከፍሉ ሆኗል ብሏል፡፡
ጥናቱ የደሞዝ ስርቆት ባልተጠበቀ መጠን መካሄዱን፣ ሰራተኞች ለማኞች እንዲሆኑና በወረርሽኙ ጊዜ ደሞዝ ወደ ቤታቸው መላክ እንዳይችሉ መሆናቸውን ይፋ አድርጓል፡፡
በኳታር 2ሚሊዮን አካባቢ ከደቡባዊ ኢሲያ የመጡ ሰራተኞች ያሉ ሲሆን አብዛኞቹ ከኳታሩ የ2022 የአለም ዋንጫ ጋር ተያያዥነት ባላቸው የግንባታ ስራ የተሰማሩ ናቸው፡፡
ምንም እንኳን የሀገሪቱ መንግስት ኩባንያዎች በለይቶ ማቆያ ለሚገኙና በመንግስት ራሳቸውን እንዲለዩ ለተገደረጉ ሰራተኞች እንዲከፍሉ ቢገደዱም ትእዛዙን ተግባራዊ ከማድረግ አንጻር በርካታ ችግር መኖሩን ጥናቱ አመልክቷል፡፡
መንግስት ሰራቸውን የሚያቆሙ ኩባንያዎች ለሰራተኞች ማስጠንቀቂያ እንዲሰጡና የጥቅማጥቅም ክፍያ አንዲያደርጉ እንደሚጠይቃቸው ጥናቱ ጠቅሷል፡፡