ፕሬዝደንት ጆ ባይደን በኔቶ ስብሰባው ወቅት የዩክሬኑን ፕሬዝደንት ቮሎድሚር ዘለንስኪን ተሳስተው ፑቲን ብለው አስተዋውቀዋቸዋል
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ባይደን በኔቶ ስብሰሳ ወቅት አዲስ ስህተት ሰሩ።
የአሜሪካ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን በትናንትናው እለት በተካሄደው የኔቶ ስብሰባው ወቅት የዩክሬኑን ፕሬዝደንት ቮሎድሚር ዘለንስኪን ተሳስተው ፑቲን ብለው አስተዋውቀዋቸዋል።
ፕሬዝደንቱ ስህታተቸውን ወዲያውኑ አስተካክለዋል።
"አሁን እድሉን ለቆራጡ የዩክሬን ፕሬዝደንት ፑቲን አሰጣለሁ" ብለዋል ባይደን ዘለንስኪን እየጠቆሙ።
ከሁለት ሰክንዶች በኋላ ስህተታቸውን ያስተካከሉት ባይደን "ፕሬዝደንት ዘለንስኪ ፕሬዝደንት ፑቲንን ታሸንፋለህ። ፑቲንን በማሸነፍ ላይ ትኩረት አደርጋለሁ"ብለዋል።
ፕሬዝደንት ባይደን ዘለንስኪን ፑቲን እያሉ ሲጠሩ ተሰብሳቢዎቹ ግራ ተጋብተው ነበር። ባይደን ይህን አስተያየት የሰጡት ለዩክሬን የሚያስፈልጋትን የጸጥታ ድጋፍ ለማድረግ ከአጋሮች ጋር አዲስ ኢንሴንቲቭ ወይም እቅድ ባስጀመሩበት ፕሮግራም ላይ ነው።
ፕሬዝደንት ዘለንስኪ "እኔ ከፑቲን እሻላለሁ" የሚል መልስ ሰጥቷል።ባይደንም ዘለንስኪ ወደ ንግግር ከመግባቱ በፊት "በደንብ ትሻለለህ" ብለው በመመለስ የተወሰኑ ተሰብሳቢዎችን አስቀዋል።
ፕሬዝደንት ባይደን ባለፈው ወር የሪፐብሊካን ተወካይ ከሆኑት ተስፈኛው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር በነበረው ክርክር ደካማ አፈጻጻም በማሳየታቸው ምክንያት በድጋሚ ለመመረጥ ባላቸው እድል ላይ የራሳቸው የዲሞክራቲክ ፓርቲ አባላት ጭምር ጥርጣሬ ውስጥ ገብተዋል።
ባይደን ከውድድሩ ገለል እንዲሉ ጫና ቢደረግባቸውም፣ የዲሞክራቲክ ፓርቲ ትክክለኛ እጩ አሳቸው እንደሆኑ እየተናገሩ ናቸው።
የጀርመኑ ፕሬዝደንት ኦላፍ ሾልዝ ስህተት ያጋጥማል ሲሉ ለባይደን ተከላክለዋል።"እያንዳንዱን ሰው ሁል ጊዜ የምትከታተል ከሆነ የአፍ ወለምታ የሚያጋጥም ነገር ነው" ብለዋል ሽሎዝ።
ባይደን ትናንት ምሽት ከባለው ህዳር ወዲህ ብቻቸውን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ስለሰሩት ስህተት ተጠይቀው ነበር። ባይደን ኔቶ በአመራርነት ዘመናቸው ኔቶ ስኬታማ ነበር ሲሉ መልሰዋል።
ይህ ስህተት ለአዛውንቱ የአሜሪኬ ፕሬዝደንት የመጀመሪያቸው አይደለም። ከሳምንት በፊት "እኔ ጥቁር ሴት ነኝ" ማለታቸው መነጋገሪያ አድርጓቸው ነበር።