ሩሲያ ኪቭ ላይ በፈጸመችው ጥቃት በህንጻዎችና በኃይል መሰረተልማቶች ጉዳት ደረሰ
የኪቭ ወታደራዊ አስተዳዳሪ እንዳሉት ከሆነ በከፍተኛ ቁጥር ከተለያየ አቅጣጫ ወደ ከተማዋ በቀረቡት ድሮኖች በተፈጸመው ጥቃት በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት የለም
ሩሲያ በዩክሬን ልዩ ያለችውን ወታደራዊ ዘመቻ ከጀመረች 34 ወራትን አስቆጥራለች
ሩሲያ በኪቭ ላይ በፈጸመችው የአየር ጥቃት በህንጻዎች፣ በመንገዶች እና በኃይል መሰረተልማቶች ላይ ጉዳት ማድረሷን የዋና ከተማዋ ወታደራዊ አስተዳደር በዛሬው እለት አስታውቋል።
አስተዳደሩ ይህን ያለው አየር ኃይሉ የድሮን ጥቃት ለመከላከል ጥረት ማድረጉን ከገለጸ በኋላ ነው።
የኪቭ ወታደራዊ አስተዳዳሪ ሴርሂ ፖፕኮ በቴሌግራም ገጻቸው እንዳሉት ከሆነ በከፍተኛ ቁጥር ከተለያየ አቅጣጫ ወደ ከተማዋ በቀረቡት ድሮኖች በተፈጸመው ጥቃት በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት የለም። ፖፕኮ እሳት መነሳቱን እና የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ወደ ቦታው መላካቸውን የሚገልጸውን ቀደም ብሎ የተፖሰተውን የከተማ አስተዳደሩን መግለጫ አስተካክለዋል።
ፕፕኮ አክለውም ሁሉም ድሮኖች ተመተው ወድቀዋል ብለዋል። ወደ ኪቭ ምን ያህል ድሮኖች እንደተተኮሱ ግልጽ አይደለም።
የተመቱት ድሮን ስብርባሪዎች በሸቭቸንኪቭስኪ እና በሆሎሲቭስኪ መንደሮች ቢያንስ የአምስት ህንጻዎች መግቢያ በሮችን መጉዳታቸውን ፖፕኮ ተናግረዋል። ጦሩ በቴሌግራም ገጹ በእሳት የተጎዱ የህንጻ በሮችን እና የኃይል መስመሮችን የሚያሳዩ ፎቶዎችን ለጥፏል።
ኪቭ እና በዙሪያ የሚገኘው ግዛት በተደጋጋሚ የአየር ጥቃት የሚፈጸምበት እና የአየር ጥቃት ማስጠንቀቂያ ደዎሎች የሚያሰሙበት ነው።
ሩሲያ በዩክሬን ልዩ ያለችውን ወታደራዊ ዘመቻ ከጀመረች 34 ወራትን አስቆጥራለች።
ዩክሬን የሩሲያን ኃይሎች ለማዛባት ኩርስክ በተባለው የሩሲያ ግዛት ጥቃት ብትከፍትም፣ የሩሲያ ኃይሎችን ወደፊት ከመገስገሰ ማስቆም አልቻለችም።
ሩሲያ በከፊል የያዘቻቸውን በምስራቅ እና ደቡብ ዩክሬን ያሉ አራት ግዛቶች ጠቅልላ ለመያዝ ዩክሬን ደግሞ የሩሲያ ኃይሎችን ከግዛቷ ለማስወጣት በማለም የሚያደርጉት ውጊያ ቀጥሏል።