የቅርብ ዘመድ የሌለው ሟች አስከሬንን ለምርምር መጠቀም እንዲቻል የሚፈቅድ ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ
አዲሱ የኢትዮጵያ ጤና አገልግሎት አዋጅ ስለ አስከሬን ጉዳይ ምን አዲስ ነገር ይዟል?
አስከሬንን ለምርምር እና ማስተማሪያነት ማዋል የሚቻለው መቼ ነው?
አዲሱ የኢትዮጵያ ጤና አገልግሎት አዋጅ ስለ አስከሬን ጉዳይ ምን አዲስ ነገር ይዟል?
ከሁለት ሳምንት በፊት የጤና አገልግሎት አስተዳደር እና ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቅረቡ ይታወሳል፡፡
ይህ ረቂቅ ከያዛቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ የአስከሬን አያያዝ እና ዝውውር ጉዳይ አንዱ ሲሆን በርካታ ጉዳዮችን ደንግጓል፡፡
ከነዚህ መካከልም በህግ ሥልጣን ከተሰጠው አካል ካልፈቀደ በስተቀር የሰው አካል ክፍልን፣ አስክሬንን ወይም አጽምን ወደ ሐገር ውስጥ ማስገባት ወይም ከሐገር ማስወጣትን ይከለክላል፡፡
እንዲሁም አስከሬንን ለማስተማሪያነት ወይም ለምርምር ማዘጋጀት የሚችለው አግባብነት ባለው አካል የተመረጠ የጤና ተቋም ነው እንደሆነም በረቂቅ አዋጁ ላይ ተጠቅሷል፡፡
ማንኛውም አስክሬንን ለማስተማሪያነት ወይም ለምርምር እንዲያዘጋጅ የተመረጠ ተቋም ያዘጋጀውን አስክሬን ከሌላ የማስተማሪያ እና የምርምር ተቋም ጋር በሚያደርገው ስምምነት መሰረት አስክሬንን ለማስተማሪያነት እና ለምርምር ተግባር እንዲውልም ይፈቅዳል፡፡
አስከሬንን ለትምህርት እና ምርምር እነማን መጠቀም የሚቻለው እንዴት እና መቼ ነው? ለሚለው ሟቹ በሕይወት በነበረበት ወቅት አግባብ ባለው አካል ፊት ሙሉ ሰውነቱን ለመለገስ ፈቃዱን ሰጥቶ ከሆነ እንደሆነ ተጠቅሷል።
ከዚህ በተጨማሪም የሟቹ የቅርብ ዘመድ ቀርቦ አስክሬኑን ለመውሰድ በሰባት ቀናት ውስጥ ካልጠየቀ ጉዳዩ የሚመለከተውን የመንግስት አካል በማሳወቅ አስከሬንን ለትምህርት ወይም ለምርምር አገልግሎት መጠቀም ይችላል ተብሏል፡፡
ይሁንና ከላይ የተጠቀሱት እንዳሉ ሆኖ አስከሬኑ ለምርምር ወይም ለተማሪዎች የተግባር ልምምድ በመዘጋጀት ላይ ባለበት ወቅት የቅርብ ዘመዱ አስክሬኑን ለመውሰድ ከጠየቀ የመውሰድ መብት እንዳለው ተገልጿል፡፡
በኢትዮጵያ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ተጋላጭ አካባቢዎች የትኞቹ ናቸው?
ረቂቅ አዋጁ አክሎም አግባብ ያለው አካል ለህብረተሰብ ጤና እና ደህንነት ስጋት የሚሆን አዲስ የተከሰተ በሽታ ምንነት፣ መንስኤ፣ ህክምና ወይም መከላከያ ለመለየት አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው የአስከሬን ምርመራ እንዲያደርግ ይፈቅዳል፡፡
አስከሬንን ለትምህርት ውይም ለምርምር ተግባር የሚጠቀም ተቋም ተግባሩን ሲያጠናቅቅ ለአስክሬን ሊሰጥ የሚገባውን ክብር ባሟላ ሁኔታ ስርዓተ ቀብር የመፈጸም ግዴታን ጥሏል፡፡
ይህ ረቂቅ አዋጅ ገና በረቂቅ ደረጃ ላይ ሲሆን በቀጣይ ተጨማሪ ውይይቶች እና ሌሎች ግብዓቶች ከታከሉበት በኋላ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከጸደቀ በኋላ እንደሚተገበር ይጠበቃል፡፡