ዛምቢያ በፈረንጆቹ 2023 ሳተላይት ልታመጥቅ መሆኑን አስታወቀች
ሙታቲ ስልጣን ከያዙ ከአንድ ወር በኋላ የ100 ቀናት የዲጂታል ልማት እቅድ ይፋ አድርገው ነበር
ዛምቢያ በፈረንጆቹ 2023 ሳተላይት ልታመጥቅ መሆኑን የሀገሪቱ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታውቋል
የዛምቢያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ፌሊክስ ሙታቲ በሰጡት መግለጫ ወደ ዲጂታል ቴክኖሎጂ መሄድ የዲጂታል ኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎችን እንደሚያሳድግ እና እንደ የአየር ንብረት ለውጥ፣ የጎርፍ መጥለቅለቅ እና የጤና ጉዳዮችን የመሳሰሉ ችግሮችን ለመቋቋም መንግስት አስቀድሞ እቅድ እንዲያወጣ ያግዛል።
ሙታቲ ሀገሪቱ ግቡን ለማሳካት በቂ እውቀት እንዳላት ተስፈኛ ነኝ ብሏል።አዲሱ መንግስት በፈረንጆቹ ነሐሴ ወር አጠቃላይ ምርጫ ካሸነፈ በኋላ ሙታቲ ባለፈው ሴፕቴምበር ላይ ስልጣን ይዘዋል፡፡
ሙታቲ ስልጣን ከያዘ ከአንድ ወር በኋላ ደቡብ አፍካዊቷ ሀገር ያላት የ100 ቀናት የዲጂታል ልማት እቅድ አቅርበው ነበር፡፡
ይህ ፕሮጀክት ተግባራዊ ከሆነ ዛምቢያን በቴክኖሎጂ ዳታ መፍትሄ ላይ ከተመሰረቱ ደቡብ አፍሪካ ሀገራት ቀዳሚ ያደርጋታል።