የሱዳን ጦር መሪ ቡርሃን ከተፋላሚያቸው ጋር "እርቅ አይኖርም" አሉ
አሜሪካ የሱዳን ጦር እና ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች የጦር ወንጀል ፈጽመዋል ሰትል ከሳቸዋለች
ቡርሃን፣ ሄሜቲ በአዲስ አበባ የፈረሙትን የተኩስ አቁም ስምምነት ውድቅ አድርገዋል
የሱዳን ጦር መሪ ጀነራል አልቡርሃን ከፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ጋር "እረቅ አይኖርም" ብለዋል።
አል ቡርሃን በጦሩ እና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ መካከል ለዘጠኝ ወራት እየተካሄደ ያለውን ጦርነት እንደሚቀጥሉ በትናንትናው እለት ዝተዋል።
የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ መሪ መሀመድ ሀምዳን ደጋሎ ወይ ሄሜቲ በዚህ ሳምንት መጀመረያ ላይ በሲቪል ጥምረቱ በቀረበው የተኩስ አቁም ሀሳብ ላይ ተስማምተው ነበር።
አሜሪካ የሱዳን ጦር እና ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች የጦር ወንጀል ፈጽመዋል ሰትል ከሳቸዋለች።
ነገርግን የሱዳን ጦር መሪ አል ቡርሃን አማጺ ሲሉ የጠሯቸው "ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች በዳርፉር እና በተቀረው የሱዳን አካባቢ የጦር ወንጀል እየፈጸሙ መሆናቸውን መላው አለም ታዝቧል። በዚህ ምክንያት ከእነሱ ስምምነት አይኖርም።" ብለዋል።
በፈረንጆቹ 2023 ሚያዝያ አጋማሽ ላይ የተጀመረው ጦርነት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንዲገደሉ እና 7.5 ሚሊዮን የሚሆኑት ደግሞ ከቤታቸው እንዲሰደዱ ምክንያት ሆኗል።
ባለፈው ወር የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ጥምረት የሆነው ኢጋድ የሁለቱን ጦር መሪዎች በአካል ለማገናኘት ጥረት ሲያደርግ ነበር።
ነገርግን ቡርሃን ባለፈው አርብ እለት ተቀናቃኛቸውን ሄሜቲን "ከሀዲ" እና "ፈሪ" በማለት ለመገናኘት ፍቃደኛ እንዳልሆኑ ገልጸዋል።
ቡርሃን፣ ሄሜቲ በአዲስ አበባ የፈረሙትን የተኩስ አቁም ስምምነት ውድቅ አድርገዋል።
ሄሜቴ በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ ከሚመራው ከሲቪል አስተዳደሩ ጥምረት ጋር በአዲስ አበባ በነበራቸው ስብሰባ፣ ንግግር ተካሂዶ ተኩስ ለማቆም ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸው ነበር።
ቡርሃን ሄሜቲን እንደሀገር መሪ ተቀብለዋል ያሏቸውን ደቡብ አፍሪካን፣ ኢትዮጵያን እና ኬንያን ተቃውመዋል።
ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ባለፈው ወር ከሱዳን በምስራቅ አቅጣጫ የምችገኘውን ገዚራ ግዛት ከያዘ እና መንደሮች ከተዘረፉ በኋላ ከባድ ህዝባዊ ተቃውሞ ገጥሞታል።
ቡርሃን ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎችን መዋጋት ለሚፈልግ ሱዳናዊ እንደሚያስታጥቁ ተናግረዋል።
አሜሪካ እና ሳኡዲ አረቢያ ሁለቱን ተፋላሚ ኃይሎች ለማስታረቅ ያደረጉት ጥረት ውጤት አላስገኘም።