ጀነራሉ ከኡጋንዳ በኋላ ወደ አዲ አበባ እንደሚመጡ ይጠበቃል
የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ አዛዥ ጀነራል መሀመድ ሀምዳን ደጋሎ በኡጋንዳ ታይተዋል፡፡
ካሳለፍነው ሚያዚያ ወር ጀምሮ ከሱዳን ብሔራዊ ጦር ጋር እየተዋጉ ያሉት የፈጥኖ ደራሽ ሀይል አዛዥ ጀነራል መሀመድ ሀምዳን ዳጋሎ ወይም ሄመቲ ወደ ኡጋንዳ አቅንተዋል፡፡
ጀነራል ሄመቲ ከኡጋንዳ ፕሬዝዳንት ዮሪ ሙሴቪኒ ጋር እንደተወያዩ የተገለጸ ሲሆን ጦርነቱን በውይይት መፍታት ስለሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ እንደተነጋገሩም ፕሬዝዳንቱ በኤክስ አካውንታቸው ላይ አስፍረዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ሙሴቪኒም ሱዳናዊን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ መሆናቸውን ገልጸው ኡጋንዳ የሱዳን ጦርነት እንዲቆም ድጋፍ እንደሚያደርጉ ለጀነራል ሄመቲ ነግረዋቸዋልም ተብሏል፡፡
የምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት (ኢጋድ) የሱዳን ጦርነት እንዲቆም ተፋላሚ ወገኖችን ፊት ለፊት ከማገናኘት ባለፈ የኬንያ፣ ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ መሪዎች መፍትሄ እንዲያፈላልጉ መሾሙ ይታወሳል፡፡
ቻድ አራት የሱዳን ዲፕሎማቶች ከሀገሪቱ እንዲወጡ አዘዘች
ኢጋድ የሱዳን ብሄራዊ ጦር አዛዥ ጀነራል አልቡርሃን እና የፈጥኖ ደራሽ ሀይሎች አዛዥ ጀነራል ሄመቲን ፊት ለፊት እንዲገናኙ ለዛሬ ቀጠሮ የነበረው ቢሆንም ይህ ፕሮግራምን ወደ ጥር ወር አሸጋግሮታል፡፡
ዘጠኝ ወር የሞላው የሱዳን ጦርነት መቋጫ እንዲያገኝ እና ወደ ስምምነት እንዲመጣ የተለያዩ አካላት ተጽዕኖ በማድረግ ላይ ቢሆኑ በጀነራል ሄመቲ የሚመራው ጦር የሱዳን ጦር ማዘዣዎችን በመቆጣጠር ላይ ይገኛል፡፡
የሀገሪቱ ጦር አዛዥ ጀነራል አልቡርሃን በበኩላቸው የጦሩ ቁልፍ ማዘዣዎች በቀላሉ በፈጥኖ ደራሽ ሀይሎች እንዲያዝ ያደረጉ አመራሮችን እንደሚቀጡ መዛታቸው ይታወሳል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ ጀነራል ሄመቲ ከኡጋንዳ ጉብኝታቸው በኋላ ወደ አዲስ አበባ ይመጣሉ ተብሎ ይገመታል፡፡