በተመድ የተመራው የሊቢያ ተኩስ አቁም ድርድር ያለስምምነት ተጠናቀቀ
በተመድ የተመራው የሊቢያ ተኩስ አቁም ድርድር ያለስምምነት ተጠናቀቀ
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) ሲመራ የነበረው የሊቢያ ተኩስ አቁም ድርድር ያለስምምነት መጠናቀቁን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡
የሊቢያ ተፋላሚ ኃይሎች በዋና ከተማዋ ትሪፖሊ ውስጥ እና አካባቢዋ በጊዜያዊነት ተኩስ እንዲያቆሙ የሚጠይቀው ለበርካታ ቀናት በተመድ አደራዳሪነት ሲካሄድ የነበረው ድርድር አልተሳካም፡፡
ሁለቱም ተፋላሚ ኃይሎች በድርድሩ መቀጠል ላይ ስለተስማሙ ተጨማሪ ድርድር በሚቀጥለው ወር ለማካሄድ የታሰበ መሆኑን የተመድ የሊቢያ ድጋፍ ሰጭ ልኡክ ቅዳሜ እለት አስታውቀዋል፡፡
የአሁኑ ተኩስ አቁም ድርድር በሩሲያና በቱርክ ሲመራ ነበር፡፡ በተኩስ አቁሙ ምክንያት ለወራት የዘለቀው ጦርነት ጋብ ቢልም፣ በሁለቱም በኩል በተደጋጋሚ ይጣስ ነበር፡፡
በኦይል የበለጸገችው ሊቢያ በሁለት ተቀናቀኝ አካላት አማካኝነት ወደ ሁለት በመከፈልና ሁለቱም አካላት በውጭ ኃይሎች በመታገዛ የሊቢያን ሀብት ለመቀራመት እያሰፈሰፉ ይገኛሉ፡፡
በተመድ የሚደገፈውና ደካማ የሆነው በጠቅላይ ሚኒስቴር ፋየዝ ሲራጂ የሚመራው መንግሰት በየጊዜው እየጠበበ ያለውን ምእራባዊ ሊቢን እንደያዘ ይገኛል፡፡ በተመድ ሀሳብ አቅራቢነት የሚካሄደው አዲሱ ድርድር በሚቀጥለው ሳምት በጄኔቫ ይካሄዳል፡፡