ማላዊ በድጋሚ ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ ልታካሄድ ነው
ማላዊ በድጋሚ ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ ልታካሄድ ነው
የማላዊ ፍርድቤት የባለፈው አመት ምርጫ ሰፊ ችግር ነበረበት በማለት ውጤቱን ከሰረዘው በኋላ ሀገሪቱ በመጭው ግንቦት ወር በድጋሚ ምርጫ እንደምታካሄድ ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡
የምርጫ ጊዜ ሰሊዳውን ያስቀመጠው የሀገሪቱ ፓርላማ ሲሆን ፓርላማው ይህን ለመወሰን የምርጫ ደንቡን አሻሽሏል፡፡
የተሻሻለው ህግ አስገላጊውን አብላጫ ድምጽ ያገኘ እጩ ከሌሌ በስተቀር ምርጫ በ30 ቀናት ውስጥ እንዲካሄድ ይፈቅዳል፡፡
ፕሬዘዳንት ፒተር ሙታሪካና የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ፍርድቤቱ ዉሳኔውን እንዲቀለብስ አቤት ብለዋል፡፡
ሙታሪካ የፓርላማውን ውሳኔ ማጽደቅ ወይንም አለማጽደቅ ወሳኔ ላይ ለመድረስ 21 ቀናት አሏቸው፡፡
የኪንያ ፍርድቤት እ.ኤ.አ. በ2017 በኬንያ የነበረውን ፕሬዘዳንታዊ ምርጫው እንዲሰረዝ ካደረገ በኃላ በአፍሪካ የምርጫ ውጤት ተሰርዞ ሲደገም ለሁለተኛ ጊዜ ነው፡፡
የማላዊ ፓርላማ የአሁኖቹ የምርጫ ኮሚሽነሮች ቢቀየሩ የሚል ኃሳብ ሰጥቷል፡፡