የሌሴቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ታባኔ ግንቦት 14 ስልጣን ይለቃሉ
ሁሉም ፓርቲዎች የገንዘብ ሚኒስትር የሆኑትን ሞከትሲ ማጃሮ ታባኔን በጊዜያዊነት እንዲተኩ ተስማምተዋል
የጠቅላይ ሚኒስትር ታባኔ ጥምረት ባለፈው ሰኞ እለት ከፈረሰ በኋላ አዲስ መንግስት እንዲመረስት በሚቀጥለው ሳምንት ስልጣን ይለቃሉ
የጠቅላይ ሚኒስትር ታባኔ ጥምረት ባለፈው ሰኞ እለት ከፈረሰ በኋላ አዲስ መንግስት እንዲመረስት በሚቀጥለው ሳምንት ስልጣን ይለቃሉ
የሌሴቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ግንቦት 14 ስልጣናቸውን በፍቃዳቸው እንደሚለቁ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቃል አቀባይ ያስታወቁ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ መልቀቂያቸውን ለንጉሱ ስለመስጠታቸው ምንም የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ገጸዋል፡፡
የታባኔ ስልጣን መልቀቅ በሀገሪቱ ባለፈው አመት የጀመረው የፖለቲካ አለመረጋጋት፤ ጸብና የፖለቲካ ሴራን እንዲሁም ከወታደሩ ጋር ያለውን ቅሬታ እንዲያባቃ ያደርጋል ተብሏል፡፡
የፈረንሳዩ የዜና ወኪል /ኤፍፒ/ ታባኔ መልቀቂያቸውን ለንጉሱ አቀርባለሁ ማለታቸውን ዘግቧል፡፡ የታባኔ ጥምረት ባለፈው ሰኞ እለት ከፈረሰ በኋላ አዲስ መንግስተት እንዲመረስት በሚቀጥለው ሳምንት ከስልጣን እንዲለቁ ይጠበቃል፡፡
ከሰኞው ክስተት በፊት፤የ80 ዓመት የእድሜ ባለጸጋ የሆኑት የሌሴቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ቶማስ ታባኔ ከአሁን በኋላ “አቅም የለኝም፤ስልጣኔን በሚመጣው ሐምሌ እለቃለሁ” አቅደው ነበር፡፡
ቃል አቀባዩ ታቦ ታካልኮኦላ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግንቦት 14 ከስልጣን እንሚለቁ ከማሳወቃቸው ውጭ ተጨማሪ መሪጃ አልሰጡም፡፡
ታባኔና የአሁኗ ሚስታቸው መሲያህ በግድያ ወንጀል ተጠርጥረው የነበረ ሲሆን ይህም በሀገሪቱ የፖለቲካ ውጥረት በመፍጠሩ ታባኔ ስልጣን እንዲለቁ ሲጠየቅ ነበር፡፡