የቻይናው ቢዋዲ ኩባንያ የዓለማችን ቁጥር አንድ መኪና ሻጭ ደረጃን ተቆናጠጠ
ለዓመታት የዓለማችን ቁጥር አንድ መኪና ሻጭ የነበረው ቴስላ ኩባንያ በቢዋይዲ ተበልጧል
ቢዋይዲ ኩባንያ ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ ከ28 ቢሊዮን ዶላር በላይ ሽያጭ አከናውኗል
የቻይናው ቢዋዲ ኩባንያ የዓለማችን ቁጥር አንድ መኪና ሻጭ ደረጃን ተቆናጠጠ።
በቻይናዋ ሸንዘን ማዕከሉን ታደረገው ቢዋይዲ የመኪና አምራች ኩባንያ አሁን ላይ በመኪና ሽያጭ የዓለማችን ቁጥር አንስ ተብሏል።
ኩባንያው ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ 1 ነጥብ 3 ሙሉ ለሙሉ እና በከፊል በኤሌክትሪክ የሚሰሩ መኪኖችን በመላው ዓለም ሸጧል።
ኩባንያው ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ 28 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዋጋ ያላቸው መኪኖችን ሸጦ 1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን ቢቢሲ ዘግቧል።
የቢዋይዲ ዋነኛ ተፎካካሪ የሆነው የአሜሪካው እና የቢሊየነሩ ኢለን መስክ ንብረት የሆነው ቴስላ ኩባንያ ደግሞ ባለፉት ሶስት ወራት 25 ቢሊዮን ዶላር ሽያጭ አከናውኗል።
ይሁንና በተጣራ ትርፍ ቴስላ ኩባንያ ከቢዋይዲ የተሻለ ትርፍ ማግኘቱ ተገልጿል።
ቴስላ ኩባንያ በቢዋይዲ የተበለጠው በቻይና ያለውን ሽያጭ ገበያ በመበለጡ እንደሆነም ተገልጿል።
በመላው ዓለም ያለው የመኪና ሽያጭ ኢንዱስትሪ እድገት አሳይቷል የተባለ ሲሆን በተለይም በከፊል በነዳጅ እና በኤሌክትሪክ ወይም ሀይብሪድ የሚባሉት መኪኖች ተፈላጊነታቸው ጨምሯል ተብሏል።
ሙሉ ለሙሉ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ከሀይብሪዶቹ ጋር ሲነጻጸሩ ርካሽ እና አነስተኛ ተፈላጊ እንደሆኑም በዘገባው ላይ ተገልጿል።