የቲክ ቶክ ባለቤት ባይቲዳንስ የሸጠውን አክሲዮን መልሶ መግዛት እንደሚፈልግ ገለጸ
ኩባንያው ቢያንስ 300 ሚሊዮን ዶላር ያለው አክሲዮን መግዛት እንደሚፈልግ ተገልጿል

ባይቲዳንስ ሸጦት የነበረውን አክሲዮን ከአማሪካ ውጭ ካሉ ሰራተኞቹ አንድ አክሲዮን በ160 ዶላር ለመግዛት ያለውን ፍላጎት አሳውቋል
የቲክ ቶክ ባለቤት ባይቲዳንስ የሸጠውን አክሲዮን መልሶ መግዛት እንደሚፈልግ ገለጸ።
የቲክ ቶክ ባለቤት የሆነው የቻይናው ባይቲዳንስ ሾጦት የነበረውን አክሲዮን ከአማሪካ ውጭ ካሉ ሰራተኞቹ አንድ አክሲዮን በ160 ዶላር ለመግዛት ያለውን ፍላጎት አሳውቋል።
ሮይተርስ እንደዘገበው ባይቲዳንስ ለአንድ አክሲዮን ያቀረበው ዋጋ ባለፈው ጥቅምት ወር ስራ ላይ ላሉት እና ለቀድሞዎቹ የአሜሪካ ሰራተኞች ካቀረበው ጋር የሚመጣጠን ነው።
ኩባንያው ቢያንስ 300 ሚሊዮን ዶላር ያለው አክሲዮን መግዛት እንደሚፈልግ ዘገባው ጠቅሷል።
የኩባንያው ጠቅላላ ሀብት 233.5 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን ይህ በአመቱ መጀመሪያ ከተቀመጠው ግምት በ26 በመቶ ያነሰ ነው። ባይቲዳንስ ባለፈው አመት ለአሜሪካ ሰራተኞቹ ባቀረበው የመልሶ መግዛት ፕሮግራም ሀብቱ 300 ቢሊዮን ደርሶ እንደነበር ተገልጿል።
ኩባንያው ለመልሶ መግዛት አሁን ለአንድ አክሲዮን ያቀረበው የ160 ዶላር ባለፈው አመት ጥር ከቀረበው የ155 ዶላር ከፍ ያለው።
የባይቲዳንስ ቃል አቀባይ ከአሜሪካ ውጭ ካሉ ሰራተኞቹ አክሲዮን መልሶ የመግዛት ፍላጎት እንዳለው አረጋግጧል። ኩባንያው ከፈረንጆቹ 2017 ጀምሮ መስፈርቱን ለሚያሟሉ ስራ ላይ ላሉ እና ለቀድሞ ሰራተኞች መልሶ የመግዛት ፕሮግራም ያቀርባል።
አሜሪካ ቲክ ቶክን ጨምሮ የቻይና የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የብሔራዊ ደህንነት አደጋ እንደሚደቅኑባት ትልጻለች፤ በዚህ የተለያዩ ጫናዎችን እያሳደረችባቸው ነው።