ቲክ ቶክ በወር 5 ዶላር ለማስከፈል እያሰበ መሆኑ ተነገረ
ቲክ ቶክ በአሁኑ ሰአት ከ18 አመት በላይ ለሆነ ሰዎች የሚሆኑ ማስታወቂያዎችን ይዞ መጥቷል
የቲክ ቶክ መተግበሪያ፣ ቲክ ቶክን ከማስታወቂያ ውጭ መጠቀም ለሚፈልጉ ደንበኞች በወር 5 ዶላር ለማስከፈል ሙከራ ጀምሯል
የቲክ ቶክ መተግበሪያ፣ ቲክ ቶክን ከማስታወቂያ ውጭ መጠቀም ለሚፈልጉ ደንበኞች በወር 5 ዶላር ለማስከፈል ሙከራ ጀምሯል።
እንደ ቢቢሲ ዘገባ የቻይናው ኩባንያ ይህን አገልግሎት የሞከረው ከአሜሪካ ውጭ ባለ እንግሊዝኛ ተናጋሪ ገበያ ላይ ነው።
የሙከራ ክፍያውም 4.99 ዶላር መሆኑ ተገልጿል።
ቀደም ሲል የአሜሪካው የቴክኖሎጂ ኩባንያ ሜታ በአውሮፖ ለሚገኙ የፌስቡክ እና ኢንስታግራም ደንበኞቹ ከአውሮፖ ህብረት የማስታወቂያ ህግ ጋር የሚጣጣም ማስታወቂያ የሌለው አገልግሎት የመጀመር ፉላጎት እንደነበረው መግለጹ ይታወሳል።
ህብረቱ ሜታ ማስታወቂያዎችን ከመልቀቁ በፊት ከተጠቃሚዎች ፍቃድ ማግኘት አለበት የሚል መመሪያ አውጥቶ ነበር።
ቲክ ቶክ በአሁኑ ሰአት ከ18 አመት በላይ ለሆነ ሰዎች የሚሆኑ ማስታወቂያዎችን ይዞ መጥቷል።
ሙከራው በትንሽ ቦታ መከናወኑን የለገጸው ቲክ ቶክ ይህ አገልግሎት በመላው አለም ስለመተግበሩ እርግጠኛ መሆን አይቻልም ብሏል።
ዩ ቲዩብ እና ቀደም ሲል ትዊተር ሲባል የነበረው ኤክስም ለሚከፍሉ ደንበኞች አገልሎቱን ያለማስታወቂያ ወይም በጥቂት ማስታወቂያ እየሰጠ ይገኛል።
የቲክ ቶክ እናት ኩባንያ ባይቲዳንስ ያገኘውን ገቢ በግልጽ ባይናርም በፈረንጆቹ 2022 85 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አግኝቷል ተብሏል።