ለቸኮሌት መስሪያ የሚውለውን ካካዎን በከፍተኛ መጠን የሚያመርቱ ሀገራት የትኞቹ ናቸው?
የተመድ የምግብ እና የእርሻ ድርጅት ባወጣው መረጃ መሰረት በ2022 የተገኘው አጠቃላይ የካካዎ ምርት መጠን 6.5 ሚሊዮን ቶን ነው
በምዕራብ አፍሪካ ያሉ ሀገራት በዓለም ካካዎን በከፍተኛ መጠን በማምረት ቀዳሚ ናቸው
በምዕራብ አፍሪካ ያሉ ሀገራት በዓለም ካካዎን በከፍተኛ መጠን በማምረት ቀዳሚ ናቸው።
ካካዎች ለተለያዩ ጣፋጭ ተኮሌቶች መስሪያ የሚሆን ዋነኛ ግብአት ነው።
ከእነዚህ ሀገራት የሚመረተው ካካዎ እንደ ኔስል፣ ማርስ፣ ኸርሺይ ላሉት ግዙፍ የምግብ ኢንዱስትሪዎች ይቀርባል። ነገርግን ለካካዎ አምራች አርሶ አደሮች የሚቀርበው የትርፍ ክፍፍል አነስተኛ መሆኑ የካከዎ ምርት በአፍሪካ የውዝግብ ምንጭ ሆኖ ቆይቷል።
የተመድ የምግብ እና የእርሻ ድርጅት ባወጣው መረጃ መሰረት በ2022 የተገኘው አጠቃላይ የካካዎ ምርት መጠን 6.5 ሚሊዮን ቶን ነው።
ከዚህ ውስጥ 60 በመቶ ወይም 3.9 ሚሊዮን ቶን የሚሆነው የተመረተው በምዕራብ አፍሪካ ሀገራት መሆኑን መረጃው ጠቅሷል።
ከምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ውስጥ ኮትዲቯር በተመሳሳይ ወቅት ባመረተችው 2.2 ሚሊዮን ቶን ቀዳሚ ነች። የኮትዲቫር ምርት የዓለምን 1/3 የሚሸፍን ነው።
ከኮትዲቯር በመቀጠል ጋና 1.1 ሚሊዮን ቶን በማምረት ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች።
ኢንዶኔዥያ በአጠቃላይ 0.667 ሚሊዮን ቶን በምረት ሶስተኛ ደረጃ የያዘች ሲሆን ኢኳዶር ደግሞ 0.337 ሚሊዮን ቶን በማምረት አራተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።
ካሜሩን፣ ናይጀሪያ፣ብራዚል እና ፔሩ በተከታታይ 0.3 ሚሊዮን ቶን፣ 0.28 ሚሊዮን ቶን፣0274 ሚሊዮን ቶን እና 0.171 ሚሊዮን ቶን በማምረት ከአራተኛ እስከ ስምንተኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል።