የካፍ ዋና ጸኃፊ በገዛ ፍቃዳቸው ስልጣናቸውን ለቀቁ
የካፍ ዋና ጸኃፊ በገዛ ፍቃዳቸው ስልጣናቸውን ለቀቁ
የአፍሪካ እግርኳስ ኮንፌደሬሽን(ካፍ) ዋና ጸኃፊ ሞውድ ሀጂ ከስልጣን መልቀቃቸውን ተከትሎ የአህጉሪቱ እግርኳስ አስተዳዳሪ አካል ቀውስ ውስጥ መግባቱን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡
አንድ አመት ላልሞላ ጊዜ ያገለገሉት ሀጂ በግል ምክንያት ስራ ማቆማቸውን ካፍ አስታውቋል፡፡
ዋና ጸኃፊው ስራቸውን የለቀቁበት ጊዜ የአፍሪካ እግርኳስ ችግር ውስጥ በገባበት ወቅት ነው ተብሏል፡፡
የቀድሞው የሞሮኮ ባለስልጣንና በሙያቸው የጥርስ ሀኪም የሆኑት ሀጂ፣ የወቅቱ የካፍ ፕሬዘዳንት አህመድ አህመድ ሙስና ሰርተዋል ብለው ለአለም አቀፉ የእግርኳስ ማህበር በማቅረባቸው ምክንያት በተባረሩት አሚር ፋህሚ ቦታ ነበር የተሾሙት፡፡
ማህበሩ በአህመድ ላይ ምርመራ መጀመሩን ቢያሳውቅም ምንም እርምጃ ሳይወስድ አንድ አመት ሆኖታል፡፡