የምስራቅ አፍሪካ አንበጣን ለመከላከል የሚያስፈልገው ወጭ ወደ 138 ሚሊዮን ዶላር ከፍ ብሏል-ተ.መ.ድ
የምስራቅ አፍሪካ አንበጣን ለመከላከል የሚያስፈልገው ወጭ ወደ 138 ሚሊዮን ዶላር ከፍ ብሏል-ተ.መ.ድ
በምስራቅ አፍሪካ ለአንበጣ መከላከል የሚውለው ወጭ በእጥፍ አድጎ 138 ሚሊዮን ዶላር መድረሱን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተ.መ.ድ.) የምግብና እርሻ ድርጅትን ጠቅሶ ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡
በቀጣይ አራት ወራት ውስጥ መንግስታት አውዳሚ ነፍሳትን ለማጥፋት ገንዘቡ ይፈልጋሉ ያለው ድርጅቱ እስካሁን የተገኘው እርዳታ 33 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ነው ብሏል፡፡
የአለም የምግብና እርሻ ድርጅት “በየቀኑ ብዙ ሀገሮች እየተጠቁ ነው፤ በዚህ ሳምንት እ.ኤ.አ ከ1994 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የአንበጣ መንጋ በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ገብቷል ብሏል፡፡
አንበጣ በኬንያ፣ በኡጋንዳ፣ በኢትዮጵያ፣ በሶማሊያና በደቡብ ሱዳን “የአመቱን አስፈላጊ ሰብል እያወደመ ” መሆኑን ድርጅቱ አስታውቋል፡፡
እንደ ድርጅቱ ከሆነ አንበጣ በምግብ ዋስትና ላይ የሚያደርሰውን ኪሳራ ለመመለስ የሚወጣው ወጭ፣ የእንበጣን መስፋፋት ለመግታት ከሚወጣው ወጭ በ15 እጥፍ ይበልጣል፡፡