ጊኒያውያን በረቂቅ-ህገመንግስት ላይ በነገው እለት ድምጽ ሊሰጡ ነው
ጊኒያውያን በረቂቅ-ህገመንግስት ላይ በነገው እለት ድምጽ ልትሰጥ ነው
በጊኒ ለወራት ከዘለቀው ተቃውሞ በኋላ ጊኒያውያን በቀረበው አዲስ የህገመንግስት ረቂቅ ላይ በነገው እለት ድምጽ እንደሚሰጡ ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡
የሀገሪቱ መንግስት እንደሚለው ከሆነ ረቂቁ ህገመንግስት ለጾታ እኩልነት ቦታ ይሰጣል፣ የሴት ልጅ ግርዛትንና ያለእድሜ ጋብቻን ያስቀራል ብሏል፡፡
ነገርግን ተችዎች የሀገሪቱ መንግስት ይህን ያደረገው የፕሬዘዳንታዊ ስልጣን ገደብን ለማራዘምና የ81 አመቱን ፕሬዘዳንት አልፋ ኮንዴን ለሶስተኛ ጊዜ ለምርጫ እንዲወዳደሩ ለማስቻል ነው ይላሉ፡፡
ምርጫው የሚካሄደው ውጥረትና ረብሻ ባለበት ወቅት ነው፡፡
13 ሚሊዮን ህዝብ ያላት ጊኒ ድሀ ሀገር ብትሆንም በተፈጥሮ በሚነራል የበለጸገች የምእራብ አፍሪካ ሀገር ነች፡፡