ሳኡዲ አረቢያ ለኡምራ ወደ ሀገሪቱ የሚገቡ ሰዎችን በጊዜያዊነት አገደች
ሳኡዲ አረቢያ ለኡምራ ወደ ሀገሪቱ የሚገቡ ሰዎችን በጊዜያዊነት አገደች
ሳኡዲ አረቢያ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ለኡምራ ጉዞ ወደ ሀገሪቱ ሰዎች እንዳይገቡ በጊዜያዊነት ማገዷን የሳኡዲ ዜና አገልግሎት ዘግቧል፡፡
የሳኡዲ አረቢያ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫው የቫይረሱ መስፋፋት አደገኛ ከሆነባቸው ሀገራት በቱሪስት ቪዛ ወደ ሀገሪቱ የሚገቡ ዜጎችና የነብዩ መሀመድን መስጅድ ለመጎብኘት የሚመጡ ሰዎች ቫይረሱ ይስፋፋል በሚል ስጋት ወደ ሳኡዲ አረቢያ እንዳይገቡ እግድ መጣሉን አስታውቀዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም የገልፍ ሀገራት ዜጎች ወደ ሳኡዲ እንዳይገቡና ከሳኡዲ ወደ ሌላ የገልፍ ሀገራት እንዳይሄዱ ታግደዋል፡፡
በሳኡዲ የጤና ባለስልጣናት የኮሮና ቫይረስን መስፋፋት በጥልቀት እየተከታተሉት መሆኑን መግለጫው ያስረዳል፡፡
የሳኡዲ መንግስት ይህን ያደረገው የቫይረሱን መስፋፋት ለመግታትና የአለም ጤና ድርጅት ቫይረሱን ለመካለከል እያደረገ ያለውን ጥረት ለማገዝ መሆኑን ገልጿል፡፡