ሀገራቱ በሚቀጥለው ወር የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎችን ማድረግ ይጠበቅባቸው ነበር
የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን (ካፍ) ስምነት የአፍሪካ ሀገራት የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎቻቸውን እንዳያደርጉ አግዷል።ፊፋ ውሳኔውን ያሳለፈው ሀገራቱ ደካማ መሰረተ ልማት ስላላቸው መሆኑን አስታውቋል።
ጅቡቲ፤ቡርኪናፋሶ፤ማላዊ፤ማሊ፤ናሚቢያ፤ ኒጀር ፤ ጊኒ ቢሳው እና ማዕከላዊ አፍሪካ በካፍ የታገዱ አገራት ናቸው።
እነዚህ የታገዱ ሀገራት የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ውድድሮችን ማካሄድ የሚያስችሉ የስታዲየም እና ሌሎች መሰረተ ልማቶች ደረጃቸውን የጠበቁ ባለመሆናቸው ቀጣይ ጨዋታዎቻቸውን በሌሎች ሀገራት እንዲያደርጉ ካፍ በአማራጭነት አስቀምጧል።
ሰሜን አፍሪካዊቷ ሞሮኮ ደቡብ አፍሪካ እና ሞሪታኒያ የታገዱት ሀገራት ውድድሮቻቸውን እንዲያካሂዱ ካፍ በመፍትሔነት አስቀምጧል።
የታገዱ ሀገራት ከዚህ በፊት የስፖርታዊ መሰረተ ልማቶቻቸውን ደረጃዎች እንዲያሻሽሉ ማስጠንቀቂያ ቢሰጥም አገራቱ ችግሩን መፍታት እንዳልቻሉ ካፍ በድረገጹ አስነብቧል።የካፍ እገዳ ውስኔ በቀጣዮቹ ሁለት ዙሮች የእግር ኳስ ማጣሪያ ውድድሮችን ብቻ እንደሚመለከትም ተገልጿል።