በአሜሪካ ሎስ አንጀለስ በተከሰተው ሰደድ አሳት ዙሪያ ምን አዳዲስ ክስተቶች አሉ?
የሞቱ ሰዎች ቁጥር ወደ 24 ሲደርስ ከ12 ሺህ በላይ መኖሪያ ቤቶችና ህንጻዎች በእሳት ተበልተዋል።
በእሳት አደጋው የደረሰው የኢኮኖሚ ጉዳት ወደ 150 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ማለቱ ተነግሯል
በአሜሪካ ሎሳንጀለስ ዙሪያ የተቀሰቀሰው ከባድ የሰደድ እሳት አደጋ ከቁጥጥር ውጪ ሆኖ ሆኖ በመቀጠል ወደ ተለያዩ አካባዎች እየተስፋፋ መሆኑ ተገልጿል።
ከባለፈው ማክሰኞ ጀምሮ በርካታ ቦታዎችን በፍጥነት ያዳረሰው በደረቅ ንፋስ እየተፋፋመ ያለው እሳት የማጥፋት ዘመቻውን ያከበደው ሲሆን ከ153 ሺህ በላይ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን ለቀው እንዲወጡ ታዘዋል።
በእሳት አደጋው የሞቱ ሰዎች ቁጥርም ወደ 24 ከፍ ማለቱ የተገለጸ ሲሆን፤ ህይወታቸው ካለፉ ሰዎች 16ቱ ኢተን አካባቢ፤ 8ቱ ደግሞ በፖሊሴድ አካባቢ መሆኑ ተገልጿል።
እሳተቱ አሁንም በርካታ ቤቶች ወደ አመድነት በመቀየር አሁን በሺዎች የሚቆጠሩ የእሳት አደጋ ሰራተኞች እና በሚሊየን የሚቆጠሩ ነዋሪዎችን እየተፈታተነ ይገኛል።
የካል ፋየር ባለስልጣን ቶድ ሆፕኪንስ ቀደም ብለው በሰጡት በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ከ8 ሺህ 900 ሄክታር በላይ መሬት ላይ ጉዳት ካደረሰው የፓሊሳዴስ እሣት ውስጥ እስካን 11 በመቶውን መቆጣጠር መቻሉን አስታውቀዋል።
እሳቱ በከፍተኛ ፍጥነት በሚጓጓ ነፋስ ከመታገዙ ጋር ተያይዞ አሁን በርካታ ስፍራዎችን ያቃጥላል በሚል የተሰጋ ሲሆን፤ በሎስ አንጀለስ ብቻ 153 ሺህ ሰዎች ከሞኖሪያቸው ለቀው እንዲወጡ ታዘዋል።
እሳቱ እየተጓጓበት ያለው ፍጥነት 57 ሺህ መኖሪያ ቤቶችን እና ህንጻችን ለአደጋ ማጋለጡም ነው የተገለጸው።
ይህንን ተከትሎም ተጨማሪ 166 ሺህ ሰዎች ከመኖሪያቸው ለመልቀቅ በተጠንቀቅ ላይ አንዲሆኑ ትእዛዝ መተላለፉም ተነግሯል።
በእሳት አደጋው ሳቢያ ቅንጡ መኖሪያ ቤቶች ጨምሮ ከ12 ሺህ በላይ መኖሪያ ቤቶችና ህንጻዎች የወደሙ ሲሆን፤ በርታ የመኖሪያ ሰፈሮች ሙሉ በሙሉ ወደ አመድነት ተቀይረዋል።
እንደ አኩዌዘር ገለፃ በሰደድ እሳት አደጋው ሳቢያ ከ250 ቢሊየን እስከ 275 ቢሊየን የሚጠጋ ገንዘብ መውደሙን ገልጿል።