ኢኮኖሚ
የአፍሪካዊያን ስደተኞች ዓመታዊ ገቢ በአሜሪካ
በአሜሪካ ከሚኖሩ አፍሪካዊያን ስደተኞች ውስጥ የደቡብ አፍሪካ ኬንያዊያን ስደተኞች ከፍተኛ ገቢ ያገኛሉ ተብሏል
ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በዓመት 72 ሺህ ዶላር በማግኘት ከአፍሪካ በሰባተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል
የአፍሪካዊያን ስደተኞች ዓመታዊ ገቢ በአሜሪካ
የዓለማችን ልዕለ ሀያል ሀገር በሆነችው አሜሪካ ኢትዮጵያዊያኑን ጨምሮ ከ4 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ አፍሪካዊያን ስደተኞች እንዳሉ የሀገሪቱ ስደተኞች ምክር ቤት ዓመታዊ ሪፖርት ያሳያል፡፡
በዚህ ተቋም ሪፖርት መሰረትም የደቡብ አፍሪካ ስደተኞች በዓመት 108 ሺህ ዶላር ገቢ በማግኘት በቀዳሚነት ተቀምጠዋል፡፡
ኑሯቸውን በአሜሪካ ካደረጉ አፍሪካዊያን መካከል የጎረቤት ሀገር ኬንያ ዜጎች ከፍተኛ ገቢ ከሚያገኙ ስደተኞች መካከል ሁለተኛ ሲሆኑ 97 ሺህ ዶላር ያገኛሉ ተብሏል፡፡
በአሜሪካ ከሚኖሩ አፍሪካዊያን ስደተኞች መካከል ከናይጀሪያ በመቀጠል በሁለተኝነት የምትገኘው ኢትዮጵያ ዜጎች ደግሞ በዓመት 72 ሺህ ዶላር እንደሚያገኙ የዚሁ ተቋም ሪፖርት 2023 ዓመት ሪፖርት ያስረዳል፡፡