በአሜሪካ ሎስ አንጀለስ በተከሰተው ሰደድ አሳት ዙሪያ ምን አዳዲስ ክስተቶች አሉ?
ከ153 ሺህ በላይ የሎስ አንጀለስ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን ለቀው እንዲወጡ ታዘዋል
የሞቱ ሰዎች ቁጥር ወደ 13 ሲደርስ ከ12 ሺህ በላይ መኖሪያ ቤቶችና ህንጻዎች በእሳት ተበልተዋል
በአሜሪካ ሎሳንጀለስ ዙሪያ የተቀሰቀሰው ከባድ የሰደድ እሳት አደጋ ከቁጥጥር ውጪ ሆኖ ሆኖ በመቀጠል ወደ ተለያዩ አካባዎች እየተስፋፋ መሆኑ ተገልጿል።
ከባለፈው ማክሰኞ ጀምሮ በርካታ ቦታዎችን በፍጥነት ያዳረሰው በደረቅ ንፋስ እየተፋፋመ ያለው እሳት የማጥፋት ዘመቻውን ያከበደው ሲሆን ከ153 ሺህ በላይ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን ለቀው እንዲወጡ ታዘዋል።
በእሳት አደጋው የሞቱ ሰዎች ቁጥርም ወደ 13 ከፍ ማለቱ የተገለጸ ሲሆን፤ በርካታ ቤቶች ወደ አመድነት በመቀየር አሁን በሺዎች የሚቆጠሩ የእሳት አደጋ ሰራተኞች እና በሚሊየን የሚቆጠሩ ነዋሪዎችን እየተፈታተነ ይገኛል።
የሰደድ እሳቱ ባለፉት 24 ሰአታት ውስጥ ተጨማሪ 400 ሄክታር መሬት ላይ በመስፋት ተጨማሪ ቤቶችን ማቃጠሉም ተነግሯ።
የካል ፋየር ባለስልጣን ቶድ ሆፕኪንስ ቀደም ብለው በሰጡት በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ከ8 ሺህ 900 ሄክታር በላይ መሬት ላይ ጉዳት ካደረሰው የፓሊሳዴስ እሣት ውስጥ እስካን 11 በመቶውን መቆጣጠር መቻሉን አስታውቀዋል።
እሳቱ በከፍተኛ ፍጥነት በሚጓጓ ነፋስ ከመታገዙ ጋር ተያይዞ አሁን በርካታ ስፍራዎችን ያቃጥላል በሚል የተሰጋ ሲሆን፤ በሎስ አንጀለስ ብቻ 153 ሺህ ሰዎች ከሞኖሪያቸው ለቀው እንዲወጡ ታዘዋል።
እሳቱ እየተጓጓበት ያለው ፍጥነት 57 ሺህ መኖሪያ ቤቶችን እ ህንጻችን ለአደጋ ማጋለጡም ነው የተገለጸው።
ይህንን ተከትሎም ተጨማሪ 166 ሺህ ሰዎች ከመኖሪያቸው ለመልቀቅ በተጠንቀቅ ላይ አንዲሆኑ ትእዛዝ መተላለፉም ተነግሯል።
በአሁኑ ጊዜ በመለው ሎስ አንሰጀለስ በ6 አቅጣጫዎች ባለው እሳት ሳቢያ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ወደ 13 ከፍ በሏል።
በእሳት አደጋው ሳቢያ ቅንጡ መኖሪያ ቤቶች ጨምሮ ከ12 ሺህ በላይ መኖሪያ ቤቶችና ህንጻዎች የወደሙ ሲሆን፤ በርታ የመኖሪያ ሰፈሮች ሙሉ በሙሉ ወደ አመድነት ተቀይረዋል።