ካምቦዲያ ሴቶችን ተሸክሞ ረጅም ሰዓት በመቆም አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን አስመዘገበች
ለ8 ሰዓት ከ20 ደቂቃ ሚስቱን ተሸክሞ የቆመው ባል የመኪና ተሸላሚ ሆኗል
ውድድሩ የሴቶች ቀንን ለማክበርና የሴቶች በወንዶች ህይወት ውስጥ ያላቸውን ሚና ለማሳየት የተካሄደ ነው
በካምቦዲያ ሴቶችን ተሸክሞ ረጅም ሰዓት በመቆም ከዚህ ቀደም ያልነበረ እና አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን አስመዘግባለች።
250 የሚጠጉ የካምቦዲያ ጥንዶች አጋራቸውን በመሸከም የዓለም ድንቃድን መዝገብ ወይም ጊነስ ወርልድ ሪከርድ ላይ ለመመዝገብት ትናንት አርብ በአንድነት በመሰባሰብ አዲስ ታሪክ አስመዝግበዋል።
እንደ ውድድሩ አዘጋጆች ገለጻ ውድድሩ የሴቶች ቀንን ለማክበርና የሴቶች በወንዶች ህይወት ውስጥ ያላቸውን ሚና ለመዘከር የተካሄደ ነው።
በውድድሩ ላይ ጥንዶቹ ሚስተሰቸውን፣ እናታቸውን፣ ሴት ልጃቸውን አሊያም በህይወታቸው ውስጥ ትልቅ ስፍራ የሚሰጧትን ሴት በመሸከም ተሳትፈዋል ነው የተባለው።
ትናንት ምሽት ላይ የተጀመረው ሴቶችን አዝሎ ረጅም ሰዓት የመቆም ውድድር እስከ ዛሬ ማለዳ መቀጠሉ የተገለጸ ሲሆን፤ ጥቂቶች በድካም ውድድሩን ቢያቀራረወጡም 245 ሰዎች ግን እስከ ፍጻሜው ቆመዋል።
በዚህም ካምቦዲያ ከዚህ ቀደም ያልነበረ እና አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን አስመዝግባለች የተባለ ሲሆን፤ በውድድ ላይ ከሌሎች የተሸለ ሰዓት ተሸክመው ለቆሙ ተወዳዳሪዎቸም የተለያዩ ሽልማቶች ተሰጥተዋል።
በዚህም መሰረት አንደኛ ለወጡት ተወዳዳሪዎች አዲስ ማዝዳ ሴዳን መኪና፣ ሁለተኛ ለወጡት ሞተር ሳይክል እንዲሁም 3ኛ ለወጡት ደግሞ የገንዘብ ሽልማት ተበርክቷል ነው የተባለው።
ሬውን ቪቼት እና ባለቤቱ ሂም ፒሴይ ውድድሩን በማሸነፍ የማዝዳ መኪና ተሸላሚ መሆን የቻሉ ሲሆን፤ ሬውን ቪቼት ሚስቱን ለ8 ሰዓት ከ20 ደቂቃ ያክል ተሸክሞ በመቆም ክብረወሰን ጭምር አስመዝግቧል።
የሁነቱ አዘጋጅ አድሚን ኪምሶንግ ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ እንዳለው፤ ዝግጅቱ የጊነስ ወርልድ ሪከርድ ላይ አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን በመሆን እውቅና አግኝቷል።
ከዚህ ቀደም በካምቦዲያ ኢነርጂ መጠጥ ቡኦስትሮንግ ስፖንሰር የተደረገው ይኸው ውድድር እ.ኤ.አ. በ2023 የተካሄደ ቢሆንም አዲስ የአለም ክብረ ወሰን ማስመዝገብ እንዳልቻለ ይታወሳል።