ልዩልዩ
የኒጀር ፕሬዝዳንት ሚኒስትሮቻቸው ሁለተኛ ሚስት እንዳያገቡ አገዱ
ፕሬዝዳንት ሞሀመድ ቦዙማ “አንድ ሰው ከአንድ በላይ ሚስት እንዲኖረው አይፈቀድም” ብለዋል
ሚኒስትሮቹ ሁለተኛ ሚስት ካገቡ ከስልጣን እንደሚነሱ ተነግሯቸዋል
የኒጀር ፕሬዝዳንት ሞሀመድ ቦዙማ ሚኒስትሮቻቸው ሁለተኛ ሚስት እንዳያገቡማገዳቸው ተስምቷል።
ፕሬዝዳንት ሞሀመድ ቦዙማ የሀገሪቱ ሚኒስትሮች ውሳኔውን ጥሰው ሁለተኛ ሚስት ካገቡ ከስልጣናቸው እንደሚነሱ አስጠንቅቀዋል።
ፕሬዝዳንቱ ሴቶች በተሰበሰቡበት መድረክ ላይ ባሰሙት ንግግር የዛሬው ውሳኔ ሀይማኖተም ይደግፈዋል አንድ ሰው ከአንድ በላይ ሚስት እንዲኖረው አይፈቀድም ሲሉ ተናግረዋል።
“ውሳኔዬ ድንገተኛ እና አደገኛ መሆኑን አውቃለሁ” ያሉት ፕሬዝዳንቱ ውሳኔውን ማክበር ግን ግዴታ ነው ብለዋል፡፡
ፕሬዝዳንቱ አክለውም “በእኔ የአስተዳድር ውስጥ የሆነ ሁሉ ሁለተኛ ሚስት እንዲያገባ አይፈቀድለትም ውሳኔውን ካላከበረ ከመንግስት መዋቅር ውስጥ መልቀቅ ግዴታው ነው” ሲሉም ገልጸዋል።
24 ሚሊየን የህዝብ ብዛት ያላት ኒጀር ውስን ሀብት እንዳላት ገልጻ የውልደት መጠኑን መቆጣጠር እንደሚገባ ፕሬዝዳንቱ ጠቅሰዋል።
ሁለተኛ ሚስት እንዳያገቡ ውሳኔ የተላለፈባቸው የኒጀር ሚኒስትሮች እስካሁን ውሳኔውን ስለመቃወማቸው ወይም ስለመደገፋቸው ያሉት ነገር እንደሌለ ተነግሯል።