አሜሪካ እና ካናዳ ጥገኛ ጠያቂዎችን ላለመቀበል ስምምነት ላይ ደረሱ
ባይደን ከትሩዶ ጋር በኢኮኖሚያዊ፣ ንግድ እና ኢሚግሬሽን ጉዳዮች ለመነጋገር በኦታዋ ካናዳ ይገኛሉ
በአሜሪካ እና ካናዳ ድንበር ላይ በርካታ ስደተኞች ያለፈቃድ ያቋርጣሉ ተብሏል
አሜሪካ እና ካናዳ ጥገኛ ጠያቂዎችን ላለመቀበል ስምምነት ላይ ደረሱ።
አሜሪካ እና ካናዳ በይፋ ባልታወቁ የድንበር ማቋረጫዎች ላይ ጥገኛ ጠያቂዎችን ላለመቀበል ስምምነት ላይ ደርሰዋል ተብሏል።
በአሜሪካ እና ካናዳ ድንበር ላይ በርካታ ቁጥር ያላቸው ስደተኞች ያለፈቃድ ሲያቋርጡ ቆይተዋል።
እርምጃው በፈረንጆቹ 2004 ከአሜሪካ ጋር በተደረሰው የጥገኝነት ስምምነት ስደተኞች የጥገኝነት ጥያቄያቸውን ማቅረብ ያለባቸውን የአካሄድ ክፍተት ይዘጋል ተብሏል።
ስምምነቱ ካናዳ ስደተኞችን በይፋ የመግቢያ ቦታዎች እንድትመልስ የሚያስችል የነበሰ ሲሆን፤ ይፋዊ ባልሆኑ መሻገሪያ ቦታዎች ላይ ግን አልነበረም።
ካናዳ በደቡብ እና መካከለኛው አሜሪካ ስደት እና ጥቃትን ሸሽተው ለሚሰደዱ 15 ሽህ ስደተኞች አዲስ የስደተኞች መርሃ ግብር መፍጠር የስምምነቱ አካል መሆኑን ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የአሜሪካ ባለስልጣናት ለሲቢኤስ ተናግረዋል።
ፕሬዝዳንት ባይደን ከትሩዶ ጋር ስለተከታታይ ኢኮኖሚያዊ፣ ንግድ እና ኢሚግሬሽን ጉዳዮች ለመነጋገር በኦታዋ ካናዳ ይገኛሉ።
ስምምነቱ በሁለቱም ሀገራት ድንበር በኩል ወደ የትኛውም አቅጣጫ የሚገቡ ጥገኛ ጠያቂዎች ወደ ኋላ መመለስ ያስችላቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።
በአሜሪካ በኩል ወደ ካናዳ የሚፈልሱ ስደተኞች ቁጥር እየጨመረ መጥቷል።
እርምጃው በኒውዮርክ ግዛት እና በኩቤክ አውራጃ መካከል ባለው መደበኛ ያልሆነ መሻገሪያ በሮክስሃም መንገድ ላይ የስደተኞችን ፍሰት ለመገደብ የተደረገው ጥረት አካል መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል።