የካናዳ አፈጉባኤ ለናዚ ለተዋጋ ወታደር እውቅና በመስጠታቸው ይቅርታ ጠየቁ
ለንግግራቸው ኃላፊነት እንደሚወስድ እና ሀሳብ ራሱን ብቻ እንደሚወክል የገለጹት ሮታ ተጸጽተው የጀዊሽ ማህበረሰብን ይቅርታ ጠይቀዋል
ከሁለት ቀናት በፊት አፈጉባኤ አንቶኒ ሮታ የ98 አመቱን ያሮስላቭ ሁንካን "የዩክሬን ጀግና" ሲሉ በፖርላማ አወድሰው ነበር
የካናዳ አፈጉባኤ ለናዚ ለተዋጋ ወታደር እውቅና በመስጠታቸው ይቅርታ ጠየቁ።
የካናዳው ሀውስ ኦፍ ኮመንክ አፈጉባኤ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ለናዚ የተዋጉትን ግለሰብ በማወደሳቸው ይቅርታ ጠይቀዋል።
ከሁለት ቀናት በፊት አፈጉባኤ አንቶኒ ሮታ የ98 አመቱን ያሮስላቭ ሁንካን "የዩክሬን ጀግና" ሲሉ በፖርላማ አወድሰው ነበር። በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ሁንካ በናዚ በዋፈን ግራንዲየር ዲቪዥን ተሳትፈው እንደነበር ይቅርታ እንዲጠየቅ የፈለገው የጀዊሽ የመብት ጠበቃ ቡድን ገልጿል።
ለንግግራቸው ኃላፊነት እንደሚወስዱ እና ሀሳብ ራሳቸውን ብቻ እንደሚወክል የገለጹት ሮታ ተጸጽተው የጀዊሽ ማህበረሰብን ይቅርታ ጠይቋል።
ሮታ ለተዋጊው እውቅና የሰጡት የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ዘለንስኪ በካናዳ ጉብኝት ካደረጉ በኋላ ነው። የጸረ-ሰሜቲዝም እንቅስቃሴዎች እየጨመሩ ባለበት ሰአት የካናዳ አፈጉባኤ ይህን ማለታቸው የጂዊሽ ማህበሰሰብን አስቆጥቷል።
በካናዳ የሩሲያ አምባሳደር ኦሌግ ስቴቫኖቭ የአፈጉባኤውን ንግግር በመቃወም ለጠቅላይ ሚኒስትር ቱሪዶ ደብዳቤ መጻፋቸው ተናግራሉ።
በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ጀዊሾች በናዚ ተጨፍጭፈዋል፤ ጀዊሾች የናዚ ስም እንዲነሳ አይፈልጉም።