ካናዳ በአሜሪካ ምርቶች ላይ የ100 ቢሊዮን ዶላር ቀረጥ ልትጥል እንደምትችል አስጠነቀቀች
የካናዳ አዲሱ የንግድ ቀረጥ ለዶናልድ ትራምፕ እቅድ ምላሽ ለመስጠት ያለመ ነው ተብሏል

ዶናልድ ትራምፕ በካናዳ ላይ የ25 በመቶ ንግድ ቀረጥ እንደሚጥሉ ማቀዳቸው ይታወሳል
ካናዳ በአሜሪካ ምርቶች ላይ የ100 ቢሊዮን ዶላር ቀረጥ ልትጥል እንደምትችል አስጠነቀቀች።
ከሁለት ቀናት በኋላ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነስ ስራ የሚጀምሩት ዶናልድ ትራምፕ ከካናዳ በሚገቡ ምርቶች ላይ ቀረጥ እንደሚጥሉ ማስጠንቀቃቸው ይታወሳል።
ዶናልድ ትራምፕ ቀረጡን የሚጥሉት ካናዳ ህገወጥ ስደተኞች እና አደገኛ ዕጾች ወደ አሜሪካ እንዲገቡ ቁጥጥር አላደረገችም በሚል ነው።
ትራምፕ አክለውም ካናዳ ወደ አሜሪካ በሚገቡ ምርቶቿ ላይ የምንጥልባትን የ25 በመቶ ቀረጥ መክፈል ካልቻለች 51ኛዋ የአሜሪካ ግዛት ትሁን ሲሉም ጠይቀዋል።
የዶኔልድ ትራምፕ አስተያየት በካናዳ ፖለቲካ አለመረጋጋት ላይ ከፍተኛ ጫና የፈጠረ ሲሆን ጠቅላይ ሚንስትር ጁስቲን ትሩዶ ስልጣን እንዲለቁ አድርጓቸዋል።
ይህ በዚህ እንዳለ የዶናልድ ትራምፕ አስተዳድር በካናዳ ምርቶች ላይ የ25 በመቶ ግብር ከጣለ ዩአጸፋ እርምጃ እንደምትወስድ ዝታለች።
ሮይተርስ እንደዘገበው ከሆነ ካናዳ ከአሜሪካ ወደ ካናዳ በሚገቡ ምርቶች ላይ የ100 ቢሊዮን ዶላር ቀረጥ እንደምታስከፍል ተገልጿል።
በካናዳ በኩል ወደ አሜሪካ የሚገቡት ስደተኞች ቁጥር በሜክሲኮ በኩል ከሚገባው ጋር አነስተኛ ነው ተብሏል።
በዚህ ምክንያትም የዶናልድ ትራምፕ አስተዳድር ባለው ልክ በካናዳ ምርቶች ላይ ቀረጥ ሊጥል እንደማይችልም በዘገባው ላይ ተጠቅሷል።
በፖለቲካ አለመረጋጋት ውስጥ ያለችው ካናዳ ከሁለት ወራት በኋላ ጊዜያዊ ጠቅላይ ሚንስትር እንደምትመርጥ ይጠበቃል።
ስልጣን እንደሚለቁ የተናገሩት ጠቅላይ ሚንስትር ትሩዶ እስከ መጪው መጋቢት ወር ድረስ በሀላፊነት እንደሚቆዩ አስታውቀዋል።