የልጆቻቸው አይን እንደሚታወር ከተነገራቸው በኋላ ዓለምን የዞሩት ቤተሰብ
ካናዳውያን ቤተሰብ ሶስት ልጆቻው በጤና እክል ምክንያት አይናቸው እንደሚታወር ተነግሯቸዋል
ቤተሰቡ የልጆቻቸው አይን ከመታወሩ በፊት ጥሩ የእይታ ትውስታ እንዲኖራቸው ዓለምን መዞርን መርጠዋል
የልጆቻው አይን እንደሚታወር የተነገራቸው የካናዳ ቤተሰብ ልጆቻቸው እይታቸውን ከማጣታቸው በፊት ዓለምን እየጎበኙ ነው።
ኤዲተህ እና ሴባስቲያን የተባሉት ካናዳውያን ጥንዶች አራት እለጆች ያላቿ ሲሆን፤ ከአራ ሶስቱ በጤና እክል ምለክንያት አይናቸው እንደሚታወር ተነግሯቸዋል።
በልጆቹ ላይ የታየው የጤና እክል ከበራሄ (ጂን) ጋር ተያይዞ የሚከሰት ሲሆን፤ ከቆይታ በኋላ አይነ ስውርነትን የሚያስከትል በሽታ በመሆኑም ይታወቃል።
ካናዳውያኑ ቤተሰብ መጀመሪያ የእይታ ችግሩን የሶስት ዓመት ልጃቸው ላይ በማየት ወደ ጤና ተቋም ከሄዱ በኋላ በተደረገ ምርመራ ከአራት ልጆቻው በሶስቱ ላይ እንዳለ ተነግሯቸዋል።
ይህንን ተከትሎም በሁኔታው የተደናገጡት ቤተሰቡ ከአንድ ውሳኔ ላይ የደረሱ ሲሆን፤ ይህም ለልጆቻው ጥሩ የእይታ ትውስታ ማስቀረት ነበር።
በዚህም ዓለምን መዞርን የመረጡት ቤተሰቦቹ፤ ልጆቹ ከዚህ በፊት በመጽሃፍ አሊያም በፊልም ላይ የሚያዩትን ስፍራ በአካል እንዲያዩ በማድረግ ላይ ናቸው።
ቤተሰቡ ከአውሮፕላን ይልቅ አብዛኛው ጊዜያቸውን በመኪና መሄድን የሚመርጡ ሲሆን፤ ይህም ልጆቻው እያዳንዱን ነገር እንዲመለከቱ ለማስቻል ነው ብለዋል።
ካናዳውያ ቤተሰብ እስካሁን ስድስት ወራትን በጉዙ ያሳለፉ ሲሆን፤ በእስካሁን ቆይታቸውም ናሚቢያ፣ ዛምቢያ፣ ታንዛኒያ፣ ቱርክ እና ኢንዶኔዥያን መጎብኘታቸው ነው የተገለፀው።
ህጻናቱ በአስካሁን ጉዟቸው ቀጭኔ፣ ዝሆን እና አንበሳን ጨምሮ በርካታ የዱር እንስሳትን እንዲሁም የተለያዩ የተፈጥሮ ውበቶችን መመልከት መቻላቸው ነው የተነገረው።