በባዶ እጅ ከነብር ጋር ታግላ ህጻን ልጇን ከመበላት ያዳነቸው ህንዳዊት እናት
ህንዳዊቷ እናት ጉዳት ቢደርስባትም የ1 ዓመት ከ3 ወር የሆነ ህጻን ልጇን ከመበላት አድናለች
“እናት ከምንም በላይ ልጇን ትወዳለች” ለሚላው ይህቺ ህንዳዊት እናት በከነብር ጋር በመፋለም አረጋግጣለች
በህንድ ማድሃያ ፓርዴሽ ግዛት አንዲት እናት ልጇን ለማዳን ስትል በባዶ እጇ ከነብር ጋር ትግል መግጠሟ የበርካቶችን ቀለብ ስቧል።
የ25 ዓመቷ እናት አርቻና ቹዳሪ “እናት ከምንም በላይ ልጇን ትዳለች” ለሚላው አባባል ማረጋገጫን የሰጠች በሚል ከበርካቶች ጀግና በሚል አድናቆት እየጎረፈላት ነው።
ነገሩ የሆነው እንዲህ ነው፤ እናት እና ልጅ ባሳለፍነው ሳምንት እሁድ ከሚኖሩበት አካባ ወደ ገጠራማ አካባ በጫካ ውስጥ እየተጓዙ ነበር፤ ታዲያ በዚህ ወቀት ጫካ ውስጥ አድፍጦ የነበረ ግዙፍ ነበር የ1 ዓመት ከ3 ወር የሆነ ህጻን ልጇ ጫናቅላት ዘሎ በመንከስ ወደ ጫካ መጎተት ይጀምራል።
በዚህ ወቅት ተደናገጠችው እናት አርቻና ቹዳሪ የራሷን ደህንነት ሙሉ በሙሉ በመርሳት ልጇን እየጎተተ ያለውን ነበር ወደ በባዶ እጇ መፋለም ገባች።
በዚህም ወጣቷ እናት በእጇ፣ በጀርባዋ እና ታፋዋ ላይ ከፍተኛ አካላዊ ጉዳት ቢደርስባትም ልጇን ከነበሩ ማስጣል መቻሏን ነው የተገለፀው።
እናት አርቻና ቹዳሪ ከነበሩ ጋር እየተጋለች በነበረችበት ወቅት ጩሀት በማሰማቷ የአካባው ነዋሪዎች ሰምተው በመድረስ በያዙት ዱላ ነበሩን እንዳባረሩላትም ኦዲቲ ሴንተራል በድረ ገጹ አስነብቧል።
ይህንን ተከትሎም እናት እና ልጅ ለህምክና ክትትል አካባያቸው ወደሚገኝ ሆስፒታል ተወስደው የህክምና ክትትል እያደረጉ መሆኑም ታውቋል።
ህጻኑ ልጅ በጭንቅላቱ ላይ መጠነኛ ጉዳት ያጋጠመ ሲሆን፤ እናቱ ላይ ግን ከበድ ያለ አካላዊ ጉዳት በመድረሱ ህክምና እየተከታተለች ነው ተብሏል።