ባል የሚፈልጉ ሴቶች ከቤተሰቦቻቸው ጋር በመሆን ወደ ገበያው ሄደው መግዛት ይችላሉ
ከ700 ለሚበልጡ ዓመታት የህንድ የቢሃር ግዛት ሴቶች እና ቤተሰቦቻቸው ባል የሚገዙበትን ልዩ የሙሽራ ገበያ እያስተናገደች ነው።
በየዓመቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ወንዶች በህንድ ቢሃር ግዛት ማዱባኒ በተባለ በአከባቢ ወደሚገኘው የገበያ ቦታ በመሄድ ፒፓል ዛፎች ስር የሚሰበሰቡ ሲሆን፤ እዛ በመሆንም ሚስት የምትሆናቸው ሴት እስክትመርጣቸው ድረስ ይጠባበቃሉ።
የሙሽራ ገበያው “ሳውራት ሜላ” ወይም “ሳባጋቺሂ” እየተባለ የሚጠራ ሲሆን፤ በዓመት አንድ ጊዜ የሚቆምና ለ9 ቀናት የሚቆይ መሆኑን ከኦዲቲ ሴንትራል ድረ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
`በራጃ ሃሪ ሲንግ የካርናት` ስርወ መንግስት ከ700 መቶ ዓመታት በፊት እንደተጀመረ የሚነገርለት ይህ የባል ገበያ ሴቶች ይሆነኛል ብለው ያመኑበትን ባል እንዲመርጡ ለማስቻል እንደተጀመረ ተግሯል።
በገበያው ባል ለመሆን ለሚቀርቡ ለእያንዳንዱ ሙሽራ የትምህርት ደረጃቸውን እና የቤተሰቡን የኑሮ ሁኔታ መሰረት ባድረገ መልኩ ዋጋ የሚቆረጥለት መሆኑም ተነግሯል።
የቢሃር ባህላዊ የሙሽራ ገበያ ኢንጂነሮች፣ ዶክተሮች እና የመንግስት ሰራተኞች በጣም እንደሚፈለጉ የሚነገር ሲሆን፤ ወጣቶች በጣም ተወዳጅ እንደሆኑ መረጃዎች ያመለክታሉ።
በባል መረጣ እና ግዢው ላይ ከሙሽሪት ይልቅ ለቤተሰቦቿ ምርጫ ቅድሚያ የሚሰጥ ሲሆን፤ በዚህም ጥሩ ልምድ ያለውን ባል በተመጣጣኝ ዋጋ በማመዛዘን የሚወሰን ይሆናል።
ምንም እንኳን ጥሎሽ በህንድ ውስጥ በይፋ ህገ-ወጥ ቢሆንም፣ አሁንም ወጣት እና ብቁ የሆኑ ዋት ያላገቡ ወንዶች ከሙሽሪት ቤተሰብ ከፍተኛ ጥሎሽ እንደሚጠይቁ ይነገራል፤ የሙሽራ ገበያው ዋነኛ ዓላምም ጥሎሽለን ለማስቀረት ያለመ ነው ተብሏል።
የሚያስገርመው በህንድ የባል ገበያ እንዳለ ሁሉ የሚስት ገበያም መኖሩ ሲሆን፤ በህንድ ሃውዳቲ ውስጥ በሚገኘው የሙሽሪት ገበያ እንደየብቃታቸው እና የቤት ስራ ችሎታቸው ለተለያዩ ዋጋዎች ተቆርጦላቸው ያገባሉ።