ከ60 በላይ ሴቶችን የገደለው ወንጀለኛ
ግለሰቡ ለፈጸማቸው ወንጀሎች የእድሜ ልክ እስር ተፈርዶበታል
ፍርደኛው በታሰረበት እስር ቤት በስለት ተወግቶ ህይወቱ አልፏል
ከ60 በላይ ሴቶችን የገደለው ወንጀለኛ
ሮበርት ፒክተን የ74 ዓመት ካናዳዊ ሲሆን በእሳማ እርባታ የሚተዳደር ጎልማሳ ነበር፡፡
በካናዳ ኮሎምቢያ እና ቫንኮቨር ተብለው በሚጠሩ አካባቢዎች በተደጋጋሚ ሰዎች ደብዛቸው ይጠፋል፡፡
ፖሊስ ለዓመታት ባደረገው ክትትልም ፒክተን አሳማዎችን በሚያረባበት ስፍራ ውስጥ የበርካታ ሰዎች አካል ተቀብሮ ያገኛል፡፡
በተደረገው ተከታታይ ምርመራም በተለያዩ ጊዜያት ደብዛቸው ጠፍቶ የነበሩ በርካታ ሰዎች በዚህ ስፍራ ተቀብረው ተገኝተዋል፡፡
ይህ ግለሰብ በተለይም ሴተኛ አዳሪዎችን እና ከ ዕጽ አዘዋወሪዎች ጋር የተያያዙ ሰዎችን እንደሚገድል በማስረጃ ተረጋግጧል፡፡
ቀስ በቀስ በተደረጉ የዘረመል ምርመራም ከ30 በላይ ሴቶች ተገድለው በዚህ የአሳማ ማርቢያ ቦታ ተቀብረው መገኘቱን ተከትሎ ፒክተን በከባድ የሰው ነብስ ግድያ ወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ ተገኝቷል፡፡
የህወሓት ታጣቂዎች በንፋስ መውጫ ከተማ በ9 ቀናት ውስጥ 71 ሴቶችን አስገድደው ደፍረዋል - አምነስቲ
የእድሜ ልክ እስር የተፈረደበት ይህ ሰው ከባድ ጥበቃ በሚደረግበት ኩቤክ ማረሚያ ቤት ውስጥ አብሮት በታሰረ ፍርደኛ ከአንድ ሳምንት በፊት በስለት ተወግቶ ህይወቱ እንዳለፈ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
በአጠቃላይ ፒክተን ከ60 በላይ ደብዛቸው የጠፉ ሴቶች ግድያ እጁ አለበት የተባለው ይህ ግለሰብ የ33ቱ ሴቶች ማንነት ተረጋግጦ ግድያውን እንደፈጸመም ተረጋግጧል ተብሏል፡፡
ግለሰቡ በፈረንጆቹ 2016 ላይ በግል ህይወቱ ላይ ያነጣጠረ እና ምንም አይነት ወንጀል እንዳልፈጸመ የሚያስረዳ መጽሃፍ በመጻፍ በአማዞን ላይ ለሽያጭ ያቀረበ ቢሆን ካናዳዊያን ባሰሙት ተቃውሞ ምክንያት መጽሃፉ እንዳይሸጥ ታ