ይህ ሩሲያዊ የሶፍትዌር ባለሙያ የመመረቂያ ጽሁፉን በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዙሪያ ሰርቷል ተብሏል
ሩሲያዊው የኮምፒውተር ባለሙያ ሴቶችን ማማለል የሚያስችል ሶፍትዌር መስራቱን ገለጸ፡፡
የ23 ዓመቱ ሩሲያዊ ወጣት አሌክሳንደር ዛዳን ከሰሞኑ የዓለም ብዙሃን መገናኛ ጣቢያዎችን ትኩረት ስቧል፡፡
ይህ የሶፍትዌር ባለሙያ ከአንድ ዓመት በፊት ይፋ የተደረገው ባለሙያ ቻትጅፒቲ የተሰኘውን አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ወይም ሰው ሰራሽ አስተውሎትን በመጠቀም ሚስት ማግኘቱ ተገልጿል፡፡
ባለሙያው ቻትጅፒቲ ስለ እሱ ባህሪ፣ ፍላጎት፣ ዝንባሌ፣እድሜ እና ሌሎች መረጃዎችን በማሰልጠን ለእሱ የምትሰማማ ፍቅረኛ እንዲፈልግለት አድርጓል ተብሏል፡፡
ቻት ጅፒቲ የተሰኘው አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በተሰጠው መረጃ እና ባገኘው ስልጠና መሰረት አሌክሳንደር ፍላጎት መሰረት የምትስማማውን እንስት ፈልጎ እንዳገናኘው ተናግሯል፡፡
ቻትጅፒቲ 5 ሺህ 239 እንስቶችን ለአሌክሳንደር አገናኝቶታል የተባለ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ ካሪና ኢምራቭና የተሰኘች እንስት ካገናኘው በኋላ አስደሳች የፍቅር ጊዜያትን እያሳለፉ እንደሆነም የሩሲያ ሚዲያዎች ዘግበዋል፡፡
ሴቶችን በመፍራት ራሱን ደብቆ የሚኖረው የ71 ዓመቱ ድንግል ሰው
ቻትጅፒቲን ተጠቅሞ ባዘጋጀው የቻት ቦት አማካኝነት ቴክኖሎጂው በራሱ ከሴቶቹ ጋር መልዕክቶችን ከተለዋወጠ በኋላ ምርጥ እና ፍቅረኛ ሊሆኑት የሚችሉ 160 ሴቶችን ከመረጠለት በኋላ አሌክሳንደር 12ቱን በአካል እንዳገኛቸውም ተናግሯል፡፡
አሌክሳንደር ዛዳን በመጨረሻም ከ12ቱ እጩ ፍቅረኞች ውስጥ ካሪና ኢምራቭናን እንደመረጠ ተገልጿል፡፡
ግለሰቡ አሁን ላይ ለፍቅረኛው ካሪና የታገቢኛለሽ ጥያቄውን አቅርቦ ተቀባይነት ማግኘቱን ተከትሎ የጫጉላ ሽርሽር ጊዜያቸውን በሆንግኮንግ እና ማካው በማሳለፍ ላይ ናቸው ተብሏል፡፡
እነዚህ አነጋጋሪ ፍቅረኞችም የፊታችን ነሀሴ ጋብቻቸውን ቤተሰቦቻቸው በተገኙበት ለመፈጸም ቀነ ቀጠሮ እንደያዙም ተገልጿል፡፡