በኢትዮጵያም ከ100 ሺህ ሰዎች ውስጥ 80 ያህሉ በካንሰር ይጠቃሉ
የዓለም ካንሰር ተጠቂዎች ቁጥር እየጨመረ ነው ተባለ።
እንደ ዓለም አቀፉ ስታስቲካ ጥናት ከሆነ አውስትራልያ በካንሰር ተጠቂዎች ቀዳሚዋ ሀገር ተብላለች
ጥናቱ የተሰራው ከ100 ሺህ ሰዎች መካከል ምን ያህል ሰዎች በካንሰር ተጠቅተዋል በሚለው ስሌት መሰራቱ ተገልጿል። በዚህ ስሌት መሰረትም በአውስትራሊያ ከ100 ሺህ ሰዎች ውስጥ 468 ሰዎች ሲጠቁ በአሜሪካ ደግሞ 419 ሰዎች በተመሳሳይ ይጠቃሉ ተብሏል።
ሶስተኛዋ ተጠቂ ሀገር ኖርዌይ ስትሆን ከ100 ሺህ ሰዎች ውስጥ 411 ያህሉ ሲጠቁ በፈረንሳይ 406 እንዲሁም በካናዳ 404 ሰዎች መጠቃታቸው ተገልጿል።በኢትዮጵያ በተመሳሳይ ከ100 ሺህ ሰዎች ውስጥ 80 ሰዎች በካንሰር እንደሚጠቁ ይሄው ተቋም አስታውቋል።