ልዩልዩ
1 ነጥብ 35 ቢሊዮን ዶላር ሎተሪ ያሸነፈው አሜሪካዊ ሚስቱ ላይ ክስ መሰረተ
ግለሰቡ ሚስቱን የከሰሰው ሎተሪ እንደደረሰኝ ለዘመዶቻችን ተናግራለች በሚል ነው
ጥንዶቹ ሚስጥራቸውን ለሰው ላለመናገር ስምምነት እንደነበራቸው ተገልጿል
1 ነጥብ 35 ቢሊዮን ዶላር ሎተሪ ያሸነፈው ግለሰብ ሚስቱ ላይ ክስ መሰረተ።
ስሙ ያልተጠቀሰ አሜሪካዊ ባሳለፍነው ጥር ወር ካይ ነበር የአንድ ነጥብ አምስት ቢሊዮን ዶላር ሎተሪ ያሸነፈው።
ይህ ገንዘብ በአሜሪካ ሎተሪ ታሪክ አራተኛው ከፍተኛ ገንዘብ ያስገኘ ሎተሪ ነበር።
ይህ ግለሰብ ከሚስቱ ጋር ሎተሪ ማሸነፉን ለማንም ላለመናገር ህጋዊ ስምምነት ተፈራርመው እንደነበር ተገልጿል።
ይሁንና ሚስትየው ለባሏ ቤተሰቦች የ1 ነጥብ 35 ቢሊዮን ዶላር ሎተሪ እንዳሸነፉ ተናግራለች ተብሏል።
የሚስትየውን መናገር ተከትሎ የባልየው ቤተሰቦች ከልጃቸው ገንዘብ እንዲሰጣቸው መጠየቅ ይጀምራሉ።
በሚስቱ ድርጊት የተበሳጨው ባልም ሚስቱ ሚስጢራቸውን ከስምምነታቸው ውጪ በማፍረሷ ካሳ እንዲከፈለው ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ወስዶታል።
ሚስቴ ሚስጥር በማውጣቷ ምክንያት ከቤተሰቦቹ የስነ ልቦና ጫና እንደደረሰበትም መናገሩን ኦዲቲ ሴንትራል አስነብቧል።
በዚህም ለደረሰበት ጉዳት ሚስቱ 100 ሺህ ዶላር ካሳ እንድትከፈለው ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።