ልዩልዩ
ለ30 ዓመታት ተመሳሳይ የሎተሪ እጣ የገዛው አሜሪካዊ በመጨረሻም የ18 ሚሊየን ዶላር አሸነፈ
የ61 ዓመቱ የእድሜ ባለጸጋ ከፈረንጆቹ 1991 ዓመት አንስቶ ለ30 ዓመታ ተመሳሳይ የሎተሪ እጣ ቁጥር ሲቆርጥ ቆይቷል
ካሸነፈው የሎተሪ ሽልማት የተወሰነውን ለበጎ አድራጎት ስራዎች እንደሚለግሰው ተናግሯል
በአሜሪካ ሚቺጋን የሚኖረው ይህ ግለሰብ ላለፉት 30 ዓመታት ተመሳሳይ የሎተሪ እጣ ሲቆርጥ ቆይቷል።
ይሁንና በመጨረሻም ይህ ግለሰብ የ18 ሚሊየን ዶላር እጣ ማሸነፉን ቢዝነስ ኢንሳይደር ዘግቧል።
የ61 ዓመቱ የእድሜ ባለጸጋ ከፈረንጆቹ 1991 ዓመት አንስቶ ተመሳሳይ የሎተሪ እጣ ቁጥር ሲቆርጥ መቆየቱ እንዳልሰለቸው ገልጿል።
የሎተሪ እጣው በወጣበት ቀን ምሽት ላይ እሱ ከቆረጠው ቲኬት ጋር ሲያስተያይ ተመሳሳይ መሆኑን ተጠራጥሮ ከ12 ጊዜ በላይ ማየቱን እና እውነት መሆኑን ሲያረጋግጥ መደንገጡን ገልጿል።
ግለሰቡ በዘንድሮው እጣ ላይ ከዚህ በፊት ያደርገው ከነበረው ተመሳሳይ እጣ ቁጥር ሌላ አዲስ የቲኬት ቁጥር ለመግዛት አስቦ እንደ ነበር ነገር ግን መልሶ ሀሳቡን እንደተወው በዘገባው ላይ ተጠቅሷል።
አሁን ባሸነፈው የሎተሪ ሽልማት የተወሰነውን ለበጎ አድራጎት ስራዎች እንደሚለግሰው የተናገረ ሲሆን ቀሪውን ግን ለራሱ ፍላጎቶች ማሟያ እንደሚያውለውም አክሏል።