የማህጸን በር ካንሰር በኢትዮጵያ
በኢትዮጵያ በየአመቱ ከ5 ሺህ በላይ ሴቶች ይሞታሉ
በሽታው አስቀድሞ በመመርመር ማዳን ቢቻልም ብዙዎች ግን ዘግይተው ወደ ህክምና እንደሚመጡ ተገልጿል
የማህጸን በር ካንሰር በኢትዮጵያ
በኢትዮጵያ በየዓመቱ በማህጸን በር ጫፍ ካንሰር ከ5ሺህ 300 በላይ ሴቶች እንደሚሞቱ ተገልጿል።
በማህጸን በር ጫፍ ካንሰር ከ7 ሺህ በላይ የሚሆኑ ሴቶች (እናቶች) የሚያዙ ሲሆን ከ5ሺህ 300 በላይ ሴቶች ደግሞ ለሞት እንደሚዳረጉ የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያስረዳል፡፡
የበሽታው መነሻ በግብረ-ስጋ ግንኙነት ጊዜ ከሰው ወደ ሰው በሚተላለፈው ሂውማን ፓፒሎማ በተባለ ቫይረስ አማካኝነት ይከሰታል ተብሏል፡፡
በኢትዮጵያ 80 በመቶ የሚሆኑ የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር ታማሚዎች ህመሙ ስር ከሰደደ በኃላ ወደ ጤና ተቋማት መሄዳቸው በበሽታው ህይወታቸው የሚያልፉ ዜጎችን ቁጥር እንዳናረው ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡
ጥቁር ሴቶች በጡት ካንሰር የመያዝ እድላቸው ከፍተኛ መሆኑን ጥናት አመላከተ
እድሜያቸው ከ20 አመት በፊት ሆነው የግብረስጋ ግንኙነት የሚጀምሩ ፤ ኤችአይቪ ኤድስ ቫይረስ በደማቸው ውስጥ ያለባቸው እና በአባላዘር በሽታ የተያዙ ሴቶች ለማህጸን በር ጫፍ ካንሰር የበለጠ ተጋላጭ ናቸውም ተብሏል።